አቡ ዳቢ በኢንቨስትመንት መሳብ የባህረ ሰላጤው ሀብታሟ ከተማ ተባለች
የአቡ ዳቢ ኢንቨስትመንት ባለስልጣን 993 ቢሊየን ዶላር ሀብት ማስመዝገቡ ተገልጿል
በ2022 ከነበሩት 60 ግዙፍ ስምምነቶች ውስጥ 26ቱ በአቡዳቢ የተደረጉ ናቸው ተብሏል
አቡ ዳቢ በኢንቨስትመንት መሳብ የባህረ ሰላጤው ሀብታሟ ከተማ ተባለች
የአቡ ዳቢ ኢንቨስትመንት ባለስልጣን በባህረ ሰላጤው ውስጥ ትልቁን መንግስታዊ ሀብት ይዟል። መዋዕለ-ነዋይ አፍሳሽ ባለስልጣኑ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጉም ተነግሯል።
በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2022 ወቅት አቡ ዳቢ ኢንቨስትመንት ባለስልጣን በመባል የሚታወቀው ሉዓላዊ ፈንድ ከነዳጅ ያገኘው ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት ለሀብቱ ድጋፍ አድርጎታል ተብሏል።
በ2022 ኩባንያዎች፣ የሪል እስቴት ወይም የመሠረተ ልማት ዝውውሮችን በመግዛት ገኖ ወጥቷል ነው የተባለው።
ትልቁ የአረብ ሉዓላዊ ፈንድ (የመንግስት የልማት ድርጅት) አቡ ዳቢ ኢንቨስትመንት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለቤትነት የተያዘ ነው።
ከመንግስት ክምችት የሚመነጨው ሀብቱ ለሀገሪቱ ምጣኔ-ሀብት እና ለዜጎች ጥቅማ አበርክቶው ትልቅ መሆኑ ተጠቁሟል።
አቡ ዳቢ ኢንቨስትመንት ባለስልጣን ትሪሊዮን ዶላር የሚያወጡ ንብረቶች ባለቤት በመሆን፤ በባህረ ሰላጤው ቀዳሚ ሉዓላዊ ፈንድ ነው። ባለስልጣኑ ቀዳሚ የሆነው 993 ቢሊየን ዶላር ሀብት በማስመዝገብ ነው።
በዓመት 56 በመቶ እድገት አለው የተባለም ሲሆን፤ ትልቁን እንቅስቃሴውን በሰሜን አሜሪካ አድርጓል።በአቡ ዳቢ ትልቁ የሉዓላዊ የሀብት ፈንድ ከቻይና በመቀጠል በዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የኖርዌይ የጡረታ ፈንድ በሀብት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲሆን፤ የቻይና ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን (ሲአይሲ) ደግሞ ይከተላል።
ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ከነበሩት 60 ግዙፍ ስምምነቶች ውስጥ 26ቱ በመካከለኛው ምስራቅ ሉዓላዊ የሀብት ፈንድ የተገደሉ ናቸውም ተብሏል።17ቱ ደግሞ የአሜሪካ ወይም የአውሮፓ ንብረቶች ናቸው።