ፖለቲካ
አረብ ኢምሬትስ በአሜሪካ ትብብር በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተሳተፈ ግለሰብ ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈች
የአቡዳቢ አቃቤ ህግ በአረብ ኢምሬትስ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የህግ ትብብር አድንቋል
ተከሳሹ በሌለበት የሶስት አመት እስራትና የሶስት ሚሊዮን ድርሃም ቅጣት ተጥሎበታል
የአቡዳቢ የገንዘብ ማጭበርበር ፍርድ ቤት የአሜሪካ ዜግነት ያለውን አሲም አብዱል ራህማን ጋፉር በታክስ ማጭበርበር እና በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወይም መኒ ላውንደሪንግ ጥፋተኛ ብሎ ወሳኔ አስተላልፏል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን የሶስት አመት እስር እና የ3 ሚሊዮን ድርሃም ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ከከሜሪካ ለአረብ ኢምሬትስ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡
ምርመራው የተካሄደው የአሜሪካ ባለስልጣናት ባደረጉት የህግ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው አቃቤ ህግ በታክስ ማጭበርበር እና ከአሜሪካ ወደ አረብ ኢምሬትስ በላከው አጠራጣሪ ገንዘብ ላይ ምርመራ መደረጉን ገልጿል፡፡
የአቡዳቢ አቃቤ ህግ ባገኘው የህግ ድጋፍና የገንዘብ ዝውውሩን ባህሪይ በመረዳት፣ተከሳሹ የገንዘብ ምንጩን ሳይጠቅስ አለምአቀፍ አጠራጣሪ የገንዘብ ዝውውር ማድረጉን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
ተከሳሹ በሌለበት የሶስት አመት እስራትና የሶስት ሚሊዮን ድርሃም ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ የአቡ ዳቢ አቃቤ ህግ አሜሪካ ተጠርጣሪው እንዲያዝ በማድረግ ያሳየችውን ትብብር አድንቋል፡፡