ፖለቲካ
የአለም መጻኢ የሃይል አማራጭ ጉባኤ በኤምሬትሷ አቡ ዳቢ እየተካሄደ ነው
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችም በጉባኤው እየተሳተፉ ይገኛሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጉባዕው ለመሳተፍ አቡ ዳቢ ናቸው
የአለም መጻኢ የሃይል አማራጭ ጉባኤ በኤምሬትሷ አቡ ዳቢ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችም በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ዋም የዜና ወኪል ዘግቧል።
- በኮፕ 28 ጉባዔ በአየር ንብረት እርምጃ ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉንም አቅሞች እንጠቀማለን- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር
- አረብ ኢምሬት ለታዳሽ ሀይል ልማት 50 ቢሊዮን ዶላር ማፍሰሷን ገለጸች
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአቡ ዳቢ እየተካሄደ ባለው የአለም መጻኢ የሃይል አማራጭ ጉባኤ እየተሳተፉ ነው።
በዛሬው እለት በተጀመረው እና ለሁለት ቀናት በተካሄደው የአለም መጻኢ ሃይል ጉባኤ ጉባኤ አለማችን የተጋረጠባትን የአየር ንብረት ለውጥ ፈተና የተመለከቱ ውይይቶች ይደረጋሉ።
በህዳር ወር 2023 መጨረሻ በሚካሄደው የኮፕ28 ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይም ምክክር እንደሚደረግ ነው የተገለጸው።
በጉባኤው ላይ የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዮን ሱክ የልን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎች ንግግር እያደረጉ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤን (ኮፕ28) የምታስተናግደው ኤምሬትስ፥ የዘላቂ እድገት ሳምንትን በተለያዩ መርሃግብሮች እያከበረች ነው።