በኮፕ 28 ጉባዔ በአየር ንብረት እርምጃ ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉንም አቅሞች እንጠቀማለን- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር
የዓለም ታዳሽ ሀይል ልማት ኤጀንሲ ጉባኤ በአቡዳቢ ተካሂዷል
አረብ ኢምሬትስ ከዓለም አቀፉ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ የቅርብ አጋር እና ጠንካራ ደጋፊ ሆና ትቀጥላች ብለዋል
በኮፕ 28 ጉባዔ ወቅት በአየር ንብረት እርምጃ ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉንም አቅሞች እንደሚጠቀሙ ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር ገለጹ።
የአረብ ኢሚሬትስ 28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ፕሬዝዳንት ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር በአቡዳቢ በተካሄደው የዓለም ታዳሽ ሀይል ልማት ኤጀንሲ ጉባኤ ንግግር አድርገዋል።
- አረብ ኢምሬት ለታዳሽ ሀይል ልማት 50 ቢሊዮን ዶላር ማፍሰሷን ገለጸች
- ኮፕ 28 ጉባኤ ምኞቶችን ወደ ተግባራዊነት የሚለውጥ ተግባራዊ ኮንፈረንስ ይሆናል- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር
ዶ/ር ሱልጣን በንግግራቸው፤ አረብ ኢምሬትስ 28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ወቅት በአየር ንብረት እርምጃ ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉንም አቅሞች እንደምትጠቀም አስታውዋል።
የአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድን በመወከል ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሱልጣን ፤ አረብ ኢሚሬትስ የዓለም አቀፉ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲየቅርብ አጋር ለመሆን ጥረቷን ትቀጥላለች ብለዋል።
"የዓለም አቀፍ ኃይል ስርዓቱን ለመለወጥ ከዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ ጋር ትብብራችንን እንቀጥላለን" ሲሉም አክለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (ኮፕ 28) ከአየር ንብረት እና ኃይል ስልት ጋር በተያያዙ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት የሚደረግበት መድረክ በመሆኑ ጠቀሜታ ወደር የለውም ተብሏል።
ዓለም በቀጣዮቹ ሰባት ዓመታት ታዳሽ ኃይል ለማምረት አሁን ካለው አቅም ከሶስት እጥፍ በላይ እንደሚፈልግ እና ዓለም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ፍጥነት መንቀሳቀስ እንዳለበትም ተናግረዋል።
ይህንን ለመተግበረምም ዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ "አስገዳጅነት ይኖረዋል" ያ ሲሆን፤ ይህንን የተፋጠነ ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ በሁሉም ዘርፎች ለመደገፍ ዝግጁ ነን ብለዋል።
ዶ/ር ሱልጣን አክለውም 28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) አረብ ኢምሬትስ በአየር ንብረት እርምጃ ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉንም አቅሞች ትጠቀማለች ብለዋል።
28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) በፈረንጆቹ ህዳር 2023 በተባበሩት አረብ ኢምሬት አዘጋጅነት በዱባይ ኤክስፖ ሲቲ ይዘጋጃል።