ኮፕ 28 ጉባኤ ምኞቶችን ወደ ተግባራዊነት የሚለውጥ ተግባራዊ ኮንፈረንስ ይሆናል- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር
አረብ ኢምሬትስ ከዓለም አቀፉ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ ጋር ያላትን አጋርነት የማጠናከር አላማ አላት ብለዋል
በፈረንጆቹ 2023 መጨረሻ ላይ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ታስተናግዳለች
28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ምኞቶችን ወደ ተግባራዊነት የሚለውጥ ተግባራዊ ኮንፈረንስ እንደሚሆን ተገለፀ።
አረብ ኢሚሬትስ 28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢርን የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ ልኡክ እና የኮፕ 28 ፐሬዝዳንት መሾሟ ይታወሳል።
የአቡ ዳቢ የዘላቂነት ሳምንት እንቅስቃሴ አካል የሆነው የአለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ ጠቅላላ ጉባኤ በተከፈተበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቅርብ አጋር ለመሆን ጥረቷን ትቀጥላለች ብለዋል።
"በዓለም ዙሪያ ባሉ ስድስት አህጉራት 50 ቢሊዮን ዶላር ለታዳሽ ኃይል አፍስሰናል" ያሉት አል ጃበር "በጸሃይ ኃይል ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት መደረግ አለበት" ብለዋል።
"የዓለም አቀፍ ኃይል ስርዓቱን ለመለወጥ ከዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ ጋር ትብብራችንን እንቀጥላለን" ሲሉም አክለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (ኮፕ 28) ከአየር ንብረት እና ኃይል ስልት ጋር በተያያዙ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት የሚደረግበት መድረክ በመሆኑ ጠቀሜታ ወደር የለውም ተብሏል።
የአለም የኃይል ጉባኤ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት በተለይም የኃይል ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለመቆጣጠር፣ የካርቦን ልቀትን ለማስወገድ እንዲሁም ለአየር ንብረት እርምጃ የሚደረጉ ጥረቶች እና ሀገራት በካርቦን ልቀቶች ላይ "የተጣራ ዜሮ" ላይ ለመድረስ በሚያደርጉት ቁርጠኝነት ላይ ያተኮረ ነው።
በፈረንጆቹ 2023 መጨረሻ ላይ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ታስተናግዳለች።