ወ/ሮ አዳነች ከነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ሲያገለግሉ ቆይተዋል
ሰኔ 14 ቀን የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት ተመሰረተ፡፡
አዲሱ የከተማዋ ምክር ቤትም ወይዘሮ አዳነች አቤቤን የከተማው ከንቲባ በማድረግ መርጧል፡፡ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን አሁንም በድጋሚ ከተማዋን በከንቲባነት እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡
ኢንጂነር ታከለ ኡማ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር በመሆን መሾማቸውን ተከትሎ ወ/ሮ አዳነች ከተማዋን እንዲመሩ መሰየማቸው ይታወሳል፡፡ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው ጉባዔም የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትን ቡዜና አልቃድርን የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባዔ በማድረግ ሾሟል፡፡
አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤም ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዳማ ከተማ ከንቲባ፤ የገቢዎች ሚኒስትር፤ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በመሆን አገልግለዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት፤ መስከረም 24፣201ዓ.ም መንግስት እንደሚመሰረት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡