ፖለቲካ
ደቡብ ሱዳን እና ማላዊ 78 ሺህ ዶዝ የኮሮና ክትባትን ሊያስወግዱ መሆኑን ገለጹ
የዓለም ጤና ድርጅት ግን ሁለቱ ሀገራት ክትባቱን እንዳያስወግዱ አስጠንቅቋል
የሁለቱ ሀገራት ጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች ግን የድርጅቱን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አድርገዋል
የደቡብ ሱዳን የኮሮና ቫይረስ ከትባት ዳይሬክተር ለሲጂቲኤን እንዳሉት ሀገራቸው 60 ሺህ ዶዝ ክትባት መጠቀም የማትፈልግ ሲሆን እንደምታስወግደው ተናግረዋል።
ሀገራቱ ክትባቱን እናስወግዳለን ያሉት የክትባቱ መጠቀሚያ ጊዜ ስላለፈ በማለፉ ምክንያት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ይሁንና የዓለም ጤና ደርጅት ደቡብ ሱዳን ክትባቱን ከማስወገዷ በፊት ተጨማሪ አሰራሮችን እንድታጤን አሳስቧል።
ድርጅቱ አክሎም ክትባቶቹ ከመወገዳቸው በፊት ከአምራች ድርጅቱ ጋር በመነጋገር ክትባቶቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ሊደረግ ይችላልም ብሏል።
ማላዊም ከአንድ ወር በፊት ከተረከበችው 360 ሺህ ዶዝ አስተራ ዘኒካ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ውስጥ 16 ሺህ ያህሉን እንደምትስወግድ ገልጻለች።
የዓለም ጤና ድርጅት ግን ክትባቶቹ ከተመረቱበት ጊዜ አንስቶ እስከ 36 ወራት ጊዜ ውስጥ ጥቅም ላይ ቢውሉ ችግር አይፈጥሩም ሲል የአፍሪካ ሀገራትን መክሯል።