ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ አይነ ስውርና አካል ጉደተኛ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቭሲቲ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ
ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ "የአይቻልም እና የአይሆንም መንፈስን መስበር ከተቻለ የማይቻል ነገር የለም " ብሏል
የገጠሙት ፈተናዎች ለበርካታ ዓመታት ትምህርት እንዲያቋርጥ ቢያስገድዱትም ህልሙን ከማሳካት አላገዱትም
ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ አይነ ስውርና አካል ጉደተኛ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቭሲቲ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ለ74ኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ ያስመርቃል።
ሰኔ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከሚመረቁ ተማሪዎች መካከል አካል ጉደተኛ የሆነው ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ አንዱ መሆኑን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ወጋየሁ በአማረኛ ቋንቋ ስነ-ጽሑፍ እና ፎክሎር ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ እና የባለብዙ ተሰጥኦ ባለቤት ታታሪ ወጣት መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
በፈተና የታጀበና በድል የተጠናቀቀ ጉዞ የማዕረግ ምሩቁን ሕይወት ይገልጻል።
የገጠሙት ፈተናዎች ለበርካታ ዓመታት ትምህርት እንዲያቋርጥ ቢያስገድዱትም ህልሙን ከማሳካት እንዳላገዱትም ነው ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ የሚናገረው።
ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ ዳግም ወደ ትምህርት አለም ተመልሶ ትምህርቱን በጥሩ ውጤት በድል ያጠናቀቀ የማዕረግ ተመራቂ መሆኑን ነው ዩኒቨርሲቲው ያስታወቀው።