የክርስትናና የእስልምና እምነት ተከታዮች በጋራ በጃን ሜዳ ጥምቀተ ባህር የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ፡፡
የጥምቀት በዓልን ውብና ማራኪ እናድርግ፣ ታቦት ማደሪያ ቦታዎችንም እናጽዳ በሚል መሪ-ቃል ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች በጃን ሜዳ የጽዳት ዘመቻው አከናውነዋል፡፡
የከተራ እና የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በተካሄደው ዘመቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ፍቅር ያሸንፋል ማህበር አባላትና ደጋፊዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የጽዳት ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
ተሳታፊዎችም ዘመቻው የክርስትናና የእስልምና እምነት ተከታዮች አንድነታቸውን እና አብሮነታቸውን ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚን እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፤ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፡፡