በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አንድ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ትናንት ምሽት ተገደለ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪ የነበረ አንድ ወጣት ትናንት ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት አራት ሰዓት ላይ በስውር በተፈጸመበት ጥቃት ህይወቱ አልፏል፡፡
ሟች ትናንት ምሽት ተወግቶ በዶርም ህንጻው አንደኛ ፎቅ ኮሪደር ላይ እንደተገኘ ከዩኒቨርሲቲው ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ተማሪው በህይወት ተገኝቶ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ቢወሰድም ከ30 ደቂቃ በኋላ በሆስፒታል ህይወቱ አልፏል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ለተማሪው ሞት ምክኒያት የሚሆን ምንም አይነት ግጭት እንዳልነበረ እና አሁንም እንደሌለ የዩነኒቨርሲቲው ህዝብ ግንኙነት ለአል-ዐይን አረጋግጧል፡፡
ከግድያው ጋር በተያያዘ 44 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በኮማንድ ፖስት ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡
ሟች ከመገደሉ በፊት የሚዝቱበት ተማሪዎች እንደነበሩ ለዩኒቨርሲቲው ዲሲፕሊን ኮሚቴ መረጃ ሰጥቶ እንደነበር ተገልቷል፡፡ በመሆኑም ኮሚቴው በወቅቱ እርምጃ ባለመውሰዱ የኮሚቴው መማክርት አባላት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተማሪዎች መካከል ናቸው፡፡
በአሁኑ ወቅትም በዩኒቨርሲቲው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያካተተ የጸጥታ አካል ጥበቃ እያደረገ ነው፡፡