የህዝብ ቁጥር መጨመር የሚያስከትለው አደጋ
በእጥፍ እየጨመረ ያለው የህዝብ ቁጥር በሰው፣ በአካባቢ እና በኢኮኖሚ ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል
የህዝብ ቁጥር መጨመር ከሚያስከትለው ችግር ውስጥ በውሃ፣ በምግብ እና ኢነርጂ ላይ የሚፈጥረው ጫና በቀዳሚነት ይጠቀሳል
የእርስበእርስ መስተጋብር እየጨመረ ባለበት አለም ውስጥ የህዝብ ቁጥር መ ጨመር አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። በእጥፍ እየጨመረ ያለው የህዝብ ቁጥር በሰው፣ በአካባቢ እና በኢኮኖ ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።
የህዝብ ቁጥር መጨመር ከሚያስከትለው ችግር ውስጥ በምግብ እ ኢነ ርጂ ላይ የሚፈጥረው ጫና በቀዳሚነት ይጠቀሳል። የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ የእነዚህ ሀብቶች ፍላጎት ስለሚጨምር እጥረ ት እንዲከሰት እና ፍትሃዊ ያልሆነ ክፍፍል እንዲኖር ምክንያት ይሆና።
ይህም በከተሞች የምግብ እጥረት እንዲኖር እና ልዩነት እንዲባባስ ያርጋ ል። በህዝብ ቁጥር እድገት የሚመጣ ከተሜነት በመሰረተ ልማቶች ላይ ጫና ያሳድራ ል፤ የህዝብ አገልግሎቶችም በቂ እንዳይሆኑ ያደርጋል።
በብዙ ቦታዎች ፈጣን የሆነ የከተማ መስፋፋት ከደረጃ በታች የሆነ የመኖሪያ መንደሮች እንዲመሰረቱ በማድረግ ማህበራዊ ቀውስን ያስከትላል።
የህዝብ ቁጥር መጨመር በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና የፍጆታ መጨመር አካባቢ እንዲበከል፣ ደን እን ዲመነጠር እና የተፈጥሮ ሀብቶቸም እንዲመናመኑ ምክንያት ይሆናል።
ከተሞች በሚስፋፉበት ወቅት ደኖች ስለሚመነጠሩ የስነህይወታዊ መዛባ ይከ ሰታል። የህዝብ ቁጥር መጨመር አሉታዊ ተጽዕኖ በአካባቢ ወይም በሀገር ድንበ አይ ወሰንም፣ ይልቁንም አለምአቀፋዊ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል።
በህዝብ ቁጥር እድገት ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን ለመፍታት መንግስታት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና አለምአቀፍ ተቋማት በጋራ መስራት ግድ ይላ ቸዋል።
ይህንን አለማድረግ ወደ አለመረጋጋት በመፍጠር እና ልዩነትን በማስፋት አ ዙሪት በማስከተል በሁላችንም ላይ ችግር ይፈጥራል።