በ2050 ከፍተኛ የህዝብ ብዛት የሚኖራቸው 10 ሀገራት
ኢትዮጵያ በ2050 የህዝብ ብዛቷ 214 ሚሊየን እንደሚደርስ ይገመታል
የአለም የስነህዝብ ቀን በየአመቱ ሀምሌ 11 ይከበራል
አለማችን ባለፉት 12 ወራት ሁለት አበይት ጉዳዮችን አስተናግዳለች።
የመጀመሪያው የአለም ህዝብ ብዛት 8 ቢሊየን መድረሱ ሲሆን፥ ሁለተኛው የህንድ ቻይናን በመብለጥ ቀዳሚዋ ባለብዙ ህዝብ ሀገር መሆን ነው።
በፈረንጆቹ 1955 2 ነጥብ 8 ቢሊየን የነበረው የአለም ህዝብ ብዛት አሁን ላይ ከሶስት እጥፍ በላይ አድጓል።
በ2050ም 9 ነጥብ 7 ቢሊየን እንደሚደርስ ነው የመንግስታቱ ድርጅት ትንበያ የሚያሳየው።
የአለም የስነህዝብ ቀን በፈረንጆቹ ሀምሌ 11 በየአመቱ የሚዘከር ሲሆን፥ በ2050 በአለማችን ከፍተኛ የህዝብ ብዛት የሚኖራቸው 10 ሀገራትም ይፋ ተደርገዋል።
ኢትዮጵያን በ9ኛ ደረጃ የሚያስቀምጣትን የህዝብ ብዛት ትንበያ ይመልከቱ፦