እስካሁን ስምንት ሀገራት የውድድሩ አስናጋጅ ሆነው ዋንጫውን ማንሳት ችለዋል
የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን አዘጋጅተው ዋንጫውን ያነሱ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በአህጉሪቱ ትልቅ ስፖርታዊ ውድድር ነው።የዋንጫ ውድድሩ አዘጋጅ ሆኖ ዋንጫውን ማንሳት ደግሞ ለሀገራት ታሪካዊ የሚባል የእግር ኳስ ስኬት ነው።
በ46 አመታት ውስጥ በተካሄዱ 33 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች አስተናጋጅ ሀገራት 11 ጊዜ ዋንጫ ያነሱ ሲሆን ይህም 33 በመቶ ይሸፍናል።
በኮትዲቮር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በርካታ ያልተጠበቁ ክስተቶችን እያስተናገደ ይገኛል።
ባሳየችው የጨዋታ አጀማመር ከምድቧ አታልፍም የተባለችው አስተናጋጇ ኮትዲቮር በአስደናቂ ሁኔታ የውድድሩን የ2021 አሸናፊ ሴኔጋልን አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅላለች።
የሩሲያው ስፑትኒክ እስካሁን የውድድሩ አስናጋጅ ሆነው ዋንጫውን ያነሱ ሀገራት ስምንት መሆናቸውን ዘርዝሯል።
1) ግብጽ
ግብጽ የአፍሪካን ዋንጫ አምስት ጊዜ አንስታለች። ግብጽ ውድድሩን አምስት ጊዜ ያስተናገደች ሲሆን የ1959ኙን፣ የ1986ቱን እና 2006ቱን አሸንፋለች።
2) ጋና
ጋና ውድድሩን አራት ጊዜ የማስተናገድ እድል ገጥሟታል። ካስተናገደቻቸው ውድድሮች ውስጥ የ1963ቱን እና 1978ቱን አሸንፋለች።
3) ሱዳን
ሱዳን ከፍተኛ ግምት የተሰጠውን የ1957ቱን 1970 ውን ጨዋታ ያስተናገደች ሲሆን የ1970ውን አሸንፋለች።
4) ቱኒዚያ
ቱኒዚያ ውድድሩን ሶስት ጊዜ አስተናግዳለች። ሰሜን አፍሪካዊቷ ቱኒዚያ በ2004 አስተናግዳ ዋንጫውን አንስታለች።
5) ናይጀሪያ
ናይጀሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድረን ሁለት ጊዜ አንስታለች። ምዕራብ አፍሪካዊቷ ናይጀሪያ በ1980 ያስተናገደችውን ውድድር አሸንፋለች።
6) ደቡብ አፍሪካ
ደቡብ አፍሪካ ወድድሩን ሶስት ጋዜ አስተናግዳለች። ካስተናገደቻቸው ውድድሮች ውስጥ በ1996 የተካሄደውን አሸንፋለች።
7) ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በ1962፣ በ1968 እና በ1976 ውድድሩን አስተናግዳለች። በ1962ቱ ውድድር የዋንጫ ባለቤት ሆናለች።
8) አልጀሪያ
አልጀሪያ በ1990 ውድድሩን አስተናግዳ ናይጀሪያን 1-0 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች።