“በዛሬው ጨዋታ ጥሩ ፍልሚያ አድርገን የተሻለ ውጤት እንደምናገኝ ተስፋ አለኝ”- አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከካሜሩን ጋር ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል
ሽመልስ በቀለ በጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ እንደማይሰለፍ አሰልጣኙ አስታውቀዋል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ከካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ጋር ዛሬ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ያደርጋል።
በአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን በኬፕቨርዴ ጋ ተጫውቶ 1ለ0 መረታቱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሰጡት መግለጫ፤ ከኬፕቭርዴ ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ መውጣቱ በዋልያዎቹ ላይ ተፅእኖ ፈጥሮ እንደነበረ አስታውሰዋል።
ሆኖም ግን ዋልያዎቹ አሁን ወደ ሙሉ አቋማቸው መመለሳቸውን በማንሳት፤ “ይህንንም በልምምድ ሜዳና በካምፕ ማየት ችለናል ብለዋል።
ይህንን ተከትሎም “ዛሬከ ካሜሮን ጋር በሚደረገው ጨዋታ የተሻለ ነገር እንደምናገኝ ተስፋ አለኝ" ሲሉም አሰልጣኝ ውበቱ ተናግረዋል።
ካሜሩን የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር ናት፤ ዛሬ ኢትዮጵያ የምታደርገው ጨዋታ በደጋፊዎቿ ፊት የሚካሄድ መሆኑ ጨዋታውን ከባድ ሊያደርገው ይችላ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ፤ “ሆኖም ግን ጥቃቅን ስህተቶችን አስወግደን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመፋለም ዝግጁ ነን" ብለዋል።
ውበቱ አክለው በካሜሩን ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ ብሔራዊ ቡድኑ የሚታወቅበትን ጨዋታ ለማሳየት እንደሚሞክሩ ጠቁመዋል።
"የእነ ሳሙዔል ኤቶ ሀገር የሆነችው ካሜሩን ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን እንዳላት እናውቃለን፤ ነገር ግን ዛሬ ከፈጣሪ ጋር ጥሩ ፍልሚያ እንደምናደርግ አስባለሁ" ሲሉም ተናግረዋል።
ከተጫዋቾች ጠና እና ጉዳት ጋር በተያያዘም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በመግለጫቸው፤ ኮቪድን በተለመከተ ተጫዋቾችን ጨምሮ ሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ከኮቪድ-19 ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ጉዳትን በተመለከተ ሽመልስ በቀለ በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፍ ተናግረዋል። ከሃገር ውጭ ከሚጫወቱት ሁለት ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሽመልስ ከትናንት በስቲያ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ውበቱ ገልጸዋል።
በከሜሩን አስተናግጅነት የእየተካሄደ ያለው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል።
በውድድሩ ላይ እየተሳተፈች ያለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከካሜሮን፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላለች።