ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ በጊኒዎች የጥሎ ማለፍ የደርቢ ፍልሚያ በ4ኛ ዳኝነት ይሳተፋሉ
34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ሲካሄዱ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከጊኒ፤ ግብጽ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ይጫወታሉ
በነገው እለትም አስተናጋጇ ኮቲዲቯር ከሴኔጋል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ።
ምሽት 2 ስአት ላይ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ጊኒ የሚጫወቱ ሲሆን፥ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በ4ኛ ዳኝነት ይሳተፋሉ።
ባምላክ በምድብ ጨዋታዎች ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከዛምቢያ እንዲሁም ካሜሮን ከጋምቢያ ጋር ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በመሐል ዳኝነት በብቃት መምራታቸው ይታወሳል።
አስተናጋጇ ኮቲዲቯር እና ናይጀሪያ ከሚገኙበት ምድብ 1 በሰባት ነጥብ በመሪነት ያጠናቀቀችው ኢኳቶሪያል ጊኒ ከምድብ 3 ምርጥ ሶስተኛ ሆና ያለፈችውን ጊኒ ትገጥማለች።
ምሽት 5 ሰዓት ላይ ግብፅ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል።
ፈርኦኖቹ ሁሉንም የምድብ ጨዋታዎች በተመሳሳይ 2 ለ2 አቻ በማጠናቀቅ በ3 ነጥብ ወደ ጥሎ ማለፉ መግባታቸውን ማረጋገጣቸው ይታወሳል።
አጥቂው ሞሀመድ ሳላህ በገጠመው ጉዳት ምክንያት የዛሬው ጨዋታም እንደሚያልፈው ቀደም ብሎ መገለጹ የሚታወስ ሲሆን፥ በምሽቱ ጨዋታም ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፈተና እንደሚገጥማቸው ይጠበቃል።
የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት መካሄድ ሲጀምሩ አንጎላ እና ናይጀሪያ ወደ ሩብ ፍጻሜው ማለፋቸው የሚታወስ ነው።
ትላንት በተደረጉት ጨዋታዎች አንጎላ እና ናይጄሪያ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ለቀጣይ ዙር ማለፋቸው ይታወሳል።
የጥሎ ማለፍ ፍልሚያዎች ነገም ቀጥለው ሲካሄዱ ሴኔጋል እና ምርጥ ሶስተኛ ሆና ያለፈችው ኮቲዲቯር ምሽት 5 ስአት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።