ናይጀሪያ እና አንጎላ ለሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አለፉ
አንጎላ ጨዋታው እንደተጀመረ ግብ ጠባቂው በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቶባት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብታ ነበር
ናይጀሪያ እና አንጎላ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ውድድር አልፈዋል
ናይጀሪያ እና አንጎላ ወደ ለሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አለፉ።
በኮትዲቮር እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ፣ ናይጀሪያ እና አንጎላ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ውድድር አልፈዋል።
ናይጀሪያ ካሜሩንን 2-0 ስታሸንፍ፣ አንጎላ ደግሞ ናሚቢያን 3-0 በማሸነፍ ነው ወደ ሩብ ፍጻሜው ማለፍ የቻሉት።
ትናንት ምሽች ሁለት ሰአት ላይ አንጎላ ጎረቤቷን ናሚቢያ ባሸነፈችበት ጨዋታ አጥቂው ገሊሰን ዳላ ሁለት ግቦች አስቆጥሯል።
በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ከፍተኛ ድል ያገኘችው አንጎላ፣ ጨዋታው እንደተጀመረ ግብ ጠባቂው በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቶባት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብታ ነበር።
ነገርግን ገሊሰን የመጀመሪያዋን ግብ በ38ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ ብዙም ሳይቆይ የናሚቢያ ተከላካይ ሉበኒ ሀውኮንጎ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ከወጣ በኋላ ጨዋታው ሊቀየር ችሏል። ተከላከዩ ከወጣ በኋላ ገልሰን ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል።
በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ማቡሉሉ ለአንጎላ ሶስተኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ናይጀሪያ ካሜሩንን ስታሸንፍ አድሞላ ሉክማን ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።
አድሞላ ሉክማን ባደረገው ጥረት ናይጀሪያ የረጅም ጊዜ ተቀናቃኟን 2-0 በማሸነፍ በቀጣይ ሳምንት መጨረሻ ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ውድድር አልፋለች።
ምሽት አምስት ሰአት በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ሉክማን የመጀመሪያውን ግብ ያስቆጠረው በ36ኛው ደቂቃ ላይ ነው።
ናይጀሪያ እና ናሚቢያን 3-0 ካሸነፈችው አንጎላ ጋር በቀጣይ ሳምንት አርብ በሩብ ፍጻው ጨዋታ ይጋጠማሉ።