ከጨዋታው በፊት ከፍተኛ ግምት የተሰጣት በምድቦ 'ኤፍ' የተደለደለችው ሞሮኮ አቻ ለመውጣት ተገዳለች
በዓለም ዋንጫ 4ኛ ሆና ያጠናቀቀችው ሞሮኮ ከዲአርሲ ጋር አቻ ተለያየች።
በኳታሩ የአለም ዋንጫ 4ኛ ሆና ያጠናቀቀችው ሞሮኮ ከዲርኮንጎ ጋር ባደረገችው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ 1-1 አቻ ተለያይታለች።
በትናንትናው እለት ስሶት የምድብ ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
ከጨዋታው በፊት ከፍተኛ ግምት የተሰጣት በምድቦ 'ኤፍ' የተደለደለችው ሞሮኮ አቻ ለመውጣት ተገዳለች።
የሞሮኮው አጥቂ አሽራፍ ሀኪሚ ጨዋታው በተጀመረ በስድስተኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሎ ነበር።
ነገር ግን በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ያባከነው የዲአርሲ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ በሲላስ ካቶሞፖ አማካኝነት እኩል የሚያደርገውን ግብ በ76ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል።
የጨዋታው ውጤት አራት ነጥብ ያላት ሞሮኮ ወደ 16ቱ ቀድሞ የመግባት እቅዷን አክሽፎታል። ዲአርሲ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታዎችን አቻ የወጣች ሲሆን ሞሮኮ ግን አራት ነጥብ በማካበቷ ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሏ ሰፊ ነው።
ታንዛኒያ እና ዛምቢያ ያካሄዱት ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ እና ጎረቤቷ ዛምቢያ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ታንዛንያ እና ዛምቢያ ባካሄዱት ጨዋታ፣ ታንዛንያ በመጀመሪያው አጋማሽ ግብ አስቆጥራለች።
በመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ያስተናገደችው ዛምቢያ አንድ ተጨዋች በቀይ ካርድ ከሜዳ ውጥቶባታል።
ዛምቢያ በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ብትገባም፣ ከእረፍት መልስ ባስቆጠረቻት አንድ ግብ ምክንያት አቻ ወጥታለች።
ምሽት አምስት ሰአት የተካሄደው የምድብ 'ኢ' ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ናሚቢያን አሸንፋለች።
በዚህ ጨዋታ አንጋፋው ተጨዋች ታምባ ዝዋኒ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ በ15 ደቃቃ ልዩነት ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ደቡብ አፍሪካ እንድትመራ አስችሏታል።
ደቡብ አፍሪካ በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር 4-ዐ በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።