ታሊባን ወደ አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ከመግባቱ ቀደም ብለው ከሀገር የወጡት ፕሬዘዳንቱ ወደ ታጃኪስታን አምርተዋል የሚል መረጃ ወጥቶ ነበር
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች(ዩኤኢ) ከሀገራቸው የተሰደዱትን የቀድሞውን የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒን መቀበሏን አስታወቀች፡፡
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ፤ ዩኤኢፕሬዝዳንቱን እና ቤተሰባቸውን “እንኳን ደህና መጡ” በሚል መቀበሏን አረጋግጧል፡፡ ሀገሪቱ ፕሬዝዳንቱን እና ቤተሰባቸውን የተቀበለችው ሰብዓዊነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ገልጻለች፡፡
ታሊባን ወደ አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ከመግባቱ ቀደም ብሎ ከሀገር ወጥተው የነበሩት አሽራፍ ጋኒ ታጃኪስታን ወደ አምርተዋል የሚል ወሬ ሲሰማ ነበር፡፡
አሜሪካ ከፍጋኒስታን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ለ20 አመታት ያህል የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረው ታሊባን በአጭር ቀናት ውስጥ ቤተመንግስት መግባት ችሏል፡፡
ታሊባን የአፍጋኒስታንን ዋና ከተማ ከመቆጣጠሩ ቀደም ብሎ ሀገሪቱን ሲመሩ የነበሩት አሽራፍ ጋኒ ወደ ጎረቤት ሀገር ሸሽተዋል፡፡
ታሊባንን በአሸባሪነት ፈርጀው፣ በአፍጋኒስታን ወታደር አሰማርተው የነበሩት አሜሪካና እንግሊዝን ጨምሮ ሌሎች የምእራባውያን ሀገራት ዲፕማቶቻቸውን በልዩ ዘመቻ ከአፍጋኒስታን ሲያስወጡ ታይተዋል፡፡
የታሊባንን ካቡል መግባት ተከትሎ በካቡል ከፍተኛ ትርምስ ተከትስቷል፤በአየርመንገድም ብዙ ሰዎች ወደ ውጭ ለመውጡት በውታደራዊ አውሮፕላን ላይ ሲንጠላጠሉ ነበር፡፡ ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ የአፍጋን ዜጎች ታሊባን ይበቀለናል በሚል ፍርሃት ውስጥ ናቸው፡፡