ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ የአፍጋን ዜጎች ታሊባን ይበቀለናል በሚል ፍርሃት ውስጥ ናቸው
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ(ዩኤኢ) በአፍጋስታን ያለውን ሁኔታ እየተከታታለች መሆኑንና ፍላጎትም እንዳላት አረጋግጣለች፡፡ ዩኤኢ በፍጋኒስታን በአስቸኳይ ሰላምና ጸጥታን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን ገልጻለች፡፡
የዩኤኢ የውጭ ጉዳይና የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሁሉም የአፍጋን ወገኖች ጸጥታ እንደሚያሰፍኑና በአፍጋኒስታን መረጋጋት እንዲያመጡ ተስፋ አለኝ ብላለች፡፡
አሜሪካ ከፍጋኒስታን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ለ20 አመታት ያህል የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረው ታሊባን በአጭር ቀናት ውስጥ ቤተመንግስት መግባት ችሏል፡፡
ታሊባን የአፍጋኒስታንን ዋና ከተማ ከመቆጣጠሩ ቀደም ብሎ ሀገሪቱን ሲመሩ የነበሩት አሽራፍ ጋኒ ወደ ጎረቤት ሀገር ሸሽተዋል፡፡
ታሊባንን በአሸባሪነት ፈርጀው፣ በአፍጋኒስታን ወታደር አሰማርተው የነበሩት አሜሪካና እንግሊዝን ጨምሮ ሌሎች የምእራባውያን ሀገራት ዲፕማቶቻቸውን በልዩ ዘመቻ ከአፍጋኒስታን ሲያስወጡ ታይተዋል፡፡
የታሊባንን ካቡል መግባት ተከትሎ በካቡል ከፍተኛ ትርምስ ተከትስቷል፤በአየርመንገድም ብዙ ሰዎች ወደ ውጭ ለመውጡት በውታደራዊ አውሮፕላን ላይ ሲንጠላጠሉ ነበር፡፡ ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ የአፍጋን ዜጎች ታሊባን ይበቀለናል በሚል ፍርሃት ውስጥ ናቸው፡፡