አፍጋኒስታናውያን አሜሪካ ዘርፋናለች ያሉትን 9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ንብረት እንድትመለስ ጠየቁ
በካቡል ጎዳናዎች ላይ ተቃውሟቸውን የገለጹት አፍጋናውያን ሰልፈኞች "ባይደን የ2022 የዓለማችን ሌባ" ሲሉም ተደምጧል
በአሜሪካ የታገደው የአፍጋኒስታን ማዕከላዊ ባንክ ንብረት በሙሉ እንዲመለስ ሲሉም ጠይቀዋል ሰልፈኞቹ
አፍጋኒስታናውያን አሜሪካ ዘርፋናለች ያለችውን ንብረቶች እንድትመልስላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኒስታናውያን በካቡል ጎዳናዎች ላይ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ፤ አሜሪካ ንብረታችንን ዘርፋለች በሚል ለላፉት 20 ዓመታት በአፍጋኒስታን በቆየውን የአሜሪካ አስተዳደር ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ሲገልጹ ተስተውሏል፡፡
- “የአሜሪካ የአፍጋኒስታን ቆይታ በአሳዛኝ ሁኔታ ነው የተቋጨው”- ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
- “አፍጋኒስታን አሁን ነጻ እና ሉዓላዊ ሀገር ነች”- ታሊባን
- ታሊባን የአፍጋኒስታን ሴቶች “ከ72 ኪሎ ሜትር በላይ ብቻቸውን እንዳይጓዙ” አገደ
የተለያዩ ባነሮች በመያዝ እንዲሁም መፈክሮች በማሰማት በካቡል ጎዳናዎችና በአፍጋኒስታን የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ተልዕኮ ቢሮ (UNAMA) አከባቢ ተቃውሟቸውን የገለጹት ሰልፈኞቹ፤ አሜሪካ በአፍጋኒስተን የፈጸመችው የንብረት ዘረፋ “ፍትሃዊ ያልሆነ እና ግልጽ ስርቆት ነው” ሲሉም አውግዘውታል፡፡
"ባይደን የ2022 የዓለማችን ሌባ"፣ "አሜሪካ አፍጋኒስታንን አወደመች" እና "አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ሀብት ትመልስ" የሚሉ መፈክሮች ሲያሰሙም ተደምጧል ሰልፈኞቹ፡፡
ዋሽንግተን 9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት የአፍጋኒስታን ንብረት ዘርፋለች የሚሉት ሰልፈኞቹ፤ በነሃሴ 2021 አጋማሽ ላይ ታሊባን ወደ ካቡል ተመልሶ በትረ ስልጣን መጨበጡን ተከትሎ በአሜሪካ የታገደው የአፍጋኒስታን ማዕከላዊ ባንክ ንብረት በሙሉ እንዲመለስ ሲሉም ጠይቀዋል።
የካቡል የገንዘብ ልውውጥ ገበያ ምክትል ሃጂ ዳአድ ጉል የአሜሪካ ድርጊት አሰሳፋሪ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡
"በእርግጥም ገንዘቡ የአፍጋኒስታንን ምንዛሪ እና የገንዘብ ምንዛሪ ክምችት መሰረት ያደረገ ነው፤ ጆ ባይደን በ9/11 ለተጎዱት ገንዘቡን ግማሹን ለመመደብ አስቧል፣ ይህ ደግሞ በጣም ጨካኝ እና ፍትሃዊ ያልሆነ ነው"ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዳአድ ጉል አክለው ድረጊቱ ሁሉንም የተባበሩት መንግስታት ደንቦች፣ የዓለም አቀፍ የንግድ ህግን እና ሁሉንም የባንክ ደንቦችን ይጥሳል እንዲሁም በዓለም አቀፍ ባንኮች መካከል ያለውን የባንክ ግንኙነት ያበላሻልም ብለዋል፡፡
"እናንተ(አሜሪካውያን) በእጃችሁ ያለውን የሌላ ሀገር ገንዘብ የማገድ እና የመጠቀም መብት ማን የሰጣችሁ? አሜሪካ ይህ መብት የላትም፤አሜሪካ አፍጋኒስታንን በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ልትከት ትፈልጋለች ሲሉም ተናገሯል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በታሊባን የሚመራው አስተዳደር ምክትል ቃል አቀባይ ኢናሙላህ ሳማንጋኒ እና የቀድሞ የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሃሚድ ካርዛይ ሁለቱም በቅርቡ የባደንን ውሳኔ ኢፍትሃዊ ሲሉ አውግዟል እንዲሁም የታገዱ ንብረቶች ወደ አፍጋኒስታን እንዲመለሱ ጠይቀዋል።
አሜሪካ የአፍጋኒስታን ማዕከላዊ ባንክ ንብረቶችን ማገዷ የ39 ሚሊዮን ዜጎች ሀገር እንደሆነች የሚነገርላት አፍጋኒስታን ለኩፉኛ የኢኮኖሚ ቀውስ እና ሰብዓዊ ቀውስ ይዳርጋታል የሚል ስጋት እንደፈጠረ ነው፡፡