የአፍሪካ ሀገራት በቡድን 20 ውስጥ በአባልነት መካተት አለባቸው- ሉላ ዳሲልቫ
የብራዚል ፕሬዝዳንት በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል
በጉባኤው የፍልስጤሙ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሲታየህ እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምትፈጽመውን ድብደባ እንድታቆም አሳስበዋል
በርከት ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በቡድን 20 ውስጥ በአባልነት መካተት አለባቸው ሲሉ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ ጥሪ አቀረቡ።
37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።
በስብሰባው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ፣ ያለ አፍሪካ ዓለም ምንም ነች ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 አባል መሆኑ እንደሚደግፉት አስታውቀዋል።
ይህ ብቻ በቂ አይደለም ያሉት ፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ፣ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የቡድኑ ቋሚ አባል መሆን እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ተቀራርባ መስራት እንደምትፈልግም ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።
አፍሪካ እና ብራዚል በመካከላቸው ያለውን የባህር ድንበር እንደ ድንብር ሳይሆን እንደ ጸጋ በመቁጠር የበለጠ ሊቀራረቡ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፍሊስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሸታይህ ፍሊስጤማውያን በእስራኤል ምክንያት ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ናቸው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በርካታ ሀገራት ጦርነቱ እንዲቆም ጥሪ ያቀርባሉ፣ ነገር ግን ከጥሪ በዘለለ እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።
ዘንድሮው የህብረቱ መሪዎች ጉባኤ ዋነኛ ትኩረቱን በትምህርት ልማት ላይ ያደርጋል።