ዝቅተኛ የእድሜ ጣራ የተመዘገበባቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናው?
የዓለም ባንክ በአፍሪካ ያለውን የእድሜ ጣራ የሚያመላክት ሪፖርት ይፋ አድርጓል
52.5 ዓመት አማካኝ የእድሜ ጣራ ያስመዘገበችው ቻድ በዝቅተኛ የእድሜ ጣራ ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች
የዓለም ባንክ የሰዎችን የእድሜ ጣራ ሪፖርት ያፋ ያደረገ ሲሆን፤ ከዚህም ውጥ በአፍሪካ ዝቅተኛ የእድሜ ጣራ የተመዘገበባቸውን ሀገራት ዝርዝር ይዘን ቀርበናል።
በዓለም ዙሪያ የሰዎች የእድሜ ጣራ እየጨመረ የመጣ መሆኑን መረጃዎች ቢያመላክቱም በግልጽ በሚታዩ ምክንያቶች ሳቢያ በሀገራት መካከል የእድሜ ጣሪያ ላይ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ይስተዋላል።
የአድሜ ጣራ ጉዳይ የእድል ሳይሆን፤ ያለው የገንዘብ መጠን፣ የጾታ እንዲሁም የምንኖርበት አካባቢ ለእድሜ ጣራ ከፍ እና ዝቅ ማለት ዋናኛ ምክንያቶች ተደርገው ተቀምጠዋል።
እንደ ዓለም ባንክ ሪፖርት ከሆነ በጤና ላይ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ የሚያፈሱ ሀገራት ውስጥ ያለው የእድሜ ጣራ ከፍተኛ ሆኖ ይመዘገባል።
ከዓለም ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በፈረንጆቹ በ2021 የዓለም አማካኝ የእድሜ ጣራ 71 ዓመት ነበር።
ከፍተኛ የእድሜ ጣራ ከተመዘገበባቸው የዓለም ሀገራት ውስጥ በእስያ እና በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ሀብታም ሀገራት ቀዳሚ ሲሆኑ፤ ጃፓን፣ ስዊዘርላንድ እና ደቡብ ኮሪያ በአማካኝ በ84 አመት እድሜ ቀዳሚ ሆነዋል።
በአፍሪካ ያለው የሀገራት አማካኝ የእድሜ ጣሪያ ከቦታ ቦታ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት አላው የተባለ ሲሆን፤ ለዚህም በምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ በቂ የሆነ የህክምና አገልግሎት አለመኖር፣ የኢኮኖሚ አቅም እና በሽታን የመከላከል አቅም ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህም መሰረት በአፍሪካ ዝቅተኛ የእድሜ ጣራ የተመዘገበባቸው 10 ሀገራት እንደሚከለው ቀርበዋል
1. ቻድ የእድሜ ጣራ 52.5 ዓመት
2. ናይጄሪያ የእድሜ ጣራ 52.7 ዓመት
3. መካከለኛ አፍሪካ የእድሜ ጣራ 53.9 ዓመት
4. ደቡብ ሱዳን የእድሜ ጣራ 55.0 ዓመት
5. ሶማሊያ የእድሜ ጣራ 55.3 ዓመት
6. ኤስዋቲኒ የእድሜ ጣራ 57.1 ዓመት
7. ማሊ የእድሜ ጣራ 58.9 ዓመት
8. ጊኒ የእድሜ ጣራ 58.9
9. ዲ.አር. ኮንጎ የእድሜ ጣራ 59.2
10. ሞዛምቢክ የእድሜ ጣራ 59.3 ዓመት