ቴዲ አፍሮ ፣ ቤቲ ጂ፣ ጉቱ አበራ፣ ሄዋን ገብረወልድ፣ ሌንጮ ገመቹ፣ ካስማስና አዲስ ለገሰ በአፍሪማ ላይ በተለያዩ ዘርፎች በእጩነት ቀርበዋል
8ኛው የመላው አፍሪካ ሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) በትናንትናው አለት በሴኔጋል ዳካር ተካሂዷል።
በዝንድሮው የመላው አፍሪካ ሙዚቃ ሽልማት ላይ ቴዲ አፍሮ ፣ ቤቲ ጂ፣ ጉቱ አበራ፣ ሄዋን ገብረወልድና ሌንጮ ገመቹና ካስማስ በአፍሪማ ላይ በተለያዩ ዘርፎች ኢትዮጵያን በመወከል በእጩነት ቀርበው ነበረ።
ምሽቱን በሴኔጋል በተካሔደው የመላው አፍሪካ ሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) በምርጥ የአፍሪካ ጃዝ ዘርፍ ኢትዮያዊው ጉቱ አበራ (ዴሚ) በተሰኘው የኦሮምኛ ዘፈኑ አሸንፏል።
ካስማሰ"ሰዋሰው" በተሰኘው ሙዚቃው የመላው አፍሪካ ሙዚቃ ሽልማት(አፍሪማ) በምስራቅ አፍሪካ ዘርፍ ሙዚቀኛ አሸናፊ መሆን ችሏል።
ካስማሰ "በሰዋሰው" ባሸነፈበት ስምንተኛው የአፍሪማ ሽልማት ቴዲ አፍሮ ፣ ቤቲ ጂ፣ ጉቱ አበራ ፣ ሄዋን ገብረወልድ እና ሌንጮ ገመቹ በተለያዩ ዘርፎች የታጩ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ቴዲ አፍሮ በ “ናዕት”፣ ቤቲ ጂ በ“ሰማይ” ፣ አዲስ ለገሰ ደግሞ ‘እንጃ’፣ ሌንጮ ፍቀሩ “ሰግሊ” በተሰኙ ዘፈኖቻው በዕጩነት ቀርበው ነበር።
የጃኖ ባንዷ ሔዋን ገብረወልድ በዓመቱ አዲስ ታዋቂ ዘርፍ “ሼሙና” በተሰኘ አልበሟ፤ ጃኖ ባንድ ደግሞ “በዘብናናው” በምርጥ የአፍሪካ ባንድ ሥር በእጩነት ቀርበዋል።
በ8ኛው የመላው አፍሪካ ሙዚቃ ሽልማትናይጄርያውያኑ አርቲስቶች አሳኪ፣ በርና ቦይ እና ዴቪዶ በርካታ ሽልማቶችን በመሰብሰብ የመድረኩ ድምቀት ሆነው አምሽተዋል።
የአይቮሪ ኮስታዊው ዲቢ ቢ “ታላ’ የተሰኘው ሙዚቃ የዓመቱ ምርጥ ዘፈን የተባለ ሲሆን፤ አርቲስቱ ዲቢ ቢ ያሸነፈበትን “ታላ’ የተሰኘው ሙዚቃውን ለእናቱ መታሰቢያ እንዲሆን አስታውቋል።