የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም እርምጃውን በደስታ ተቀብሏል
ደቡብ ኮሪያ አፍሪካ በሩዝ ምርቶች ላይ ጥገኝነቷን እንድታቆም ልታግዝ ነው።
ደቡብ ኮሪያ የሩዝ ምርትን ለማሳደግና ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቅረፍ ከስምንት የአፍሪካ ሀገራት ልትፈራረም ነው።
እርምጃው የመጣው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የደቡብ ኮሪያን የውጭ ፖሊሲ ለማሻሻልና በዓለም ዙሪያ የበለጠ ንቁ ሚና በመጫወት "ዓለም አቀፋዊ ሀገር" ለመሆን ቃል በመግባታቸው ነው።
በ"ኮሪያ የሩዝ ትስስር ፕሮጀክት" ደቡብ ኮሪያ በጋና፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ጋምቢያ፣ ሴኔጋል፣ ካሜሩን፣ ኡጋንዳ እና ኬንያ ተካተዋል።
ሀገሪቱ ከአካባቢው ሁኔታ ጋር የሚስማማ እና ከሁለት እስከ ሶስት እጥፍ ምርት የሚሰጡ የሩዝ ዘሮችን በማምረት ትሰራለች ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያ የግብርና ሚንስትር ቹንግ ኋንግ-ኪን ካለፈው ዓመት መገባደጃ ጀምሮ በአፍሪካ የተለያዩ ጉብኝታቸው እርዳታ እንደተጠየቁ ተናግረዋል።
ሩዝ በምዕራብ አፍሪካ ዋነኛ ምግብ መሆኑን የጠቀሰው ሮይተርስ፤ የሀገር ውስጥ ምርት 60 በመቶ የሚጠጋ ፍላጎትን ብቻ እንደሚያሟላ ጠቁሟል።
አንድ የግብርና ሚንስቴር ባለስልጣን ደቡብ ኮሪያ ለምግብ ፕሮጀክቱ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ከ77 ሚሊየን ዶላር በላይ ለማውጣት አቅዳለች።
ሀገሪቱ ከ2027 ጀምሮ በየዓመቱ 10 ሽህ ቶን የሩዝ ዘር ለማከፋፈል መወጠኗም ተነግሯል።
ስምንቱ የአፍሪካ ሀገራት የግብርና ሚንስትሮች ሴኡልን በመጎብኘት ስምምነቱን ሰኞ ይፈራረማሉ ተብሏል።
የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም እርምጃውን በደስታ ተቀብሏል።