የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንር ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ሆኑ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንር ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ሆኑ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡ ምንምእንኳን ነፃ ቢሆኑም ለ14 ቀናት ራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩ ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል፡፡
ሊቀመንበሩ በትናንትናው እለት የስራ ባልደረቦቻቸው በኮሮና ቫረስ ምክንያት ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለይተው ማስቀመጣቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸው ነበር፡፡
ከቻይናዋ ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን ከ23ሺ በላይ የሆኑ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆኗል፡፡ በሰው ህይወት ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ያለው ኮሮና ቫይረስ የአለም ኢኮኖሚንም እየጎዳው ይገኛል፡፡ የቡድን 20 ሀገራት በቫይረሱ ምክንያት እየተጎዳ ያለውን የአለም ኢኮኖሚ ለመታደግ 5 ትሪሊዮን ዶላር ወደ ኢኮኖሚው ለመልቀቅ ቃል መድበዋል፡፡