የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ
የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ
የሚኒስትሮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 17ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ስራቸውን ከነገ መጋቢት 16/2012 ጀምሮ ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ፡፡
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስርጭት ሊያስከትል በሚችለው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጽእኖ ላይ ትኩረት አድርጎ የተወያየው ምክር ቤቱ ከቤታቸው ሆነው የሚሰሩ መንግስት ሰራተኞች በየሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚወጣ ደንብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ማን ከቤት ሆኖ እንደሚሰራ ለሰራተኞቻቸው የሚያሳውቁ ይሆናል፡፡ ይህ ውሳኔ የተወሰነው በመላው አዲስ አበባ የሚካሄድ እንቅስቃሴን እና የትራንስፖርት መጨናነቅን ለመቀነስ ታስቦ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያወጣው መግለጫ ያሳያል፡፡