በቻይና የአፍሪካ አምባሳደሮች በአፍሪካውያን አያያዝ ላይ ቅሬታ አሰሙ
በቅርቡ በጓንዙ በሚኖሩ አፍሪካውያን በአከራዮቻቸው ከሚኖሩበት ቤት እንዲወጡ እየተደረጉ ነው የሚል ቅሬታ እየተሰማ ነው
የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች በቻይናዋ ጓንዙ በአፍሪካውያን ላይ በሚደርሰውን “ማግለል” ቅሬታቸውን አሰሙ
የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች በቻይናዋ ጓንዙ በአፍሪካውያን ላይ በሚደርሰውን “ማግለል” ቅሬታቸውን አሰሙ
በቻይና የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች በቻይና ጓንዙ ግዛት በሚገኙ አፍሪካውያን ላይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ መገለል እየደረሰባቸው ነው በማለት ለቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቅሬታ ማስገባታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በተናጠል ጭምር ቻይና በተለይ በደቡባዊቷ ከተማ ጓንዙ በአፍሪካውያን ላይ የሚደርሰውን ማግለልና መተንኮስ በሚመለከት መልስ እንድትሰጣቸው ይፈልጋሉ፡፡
ኮሮና ቫይረስ አሁን ከ200 በላይ ሀገራት ተከስቶ የሁሉም ስጋት ከመሆኑ በፊት ባለፈው ታህሳስ ወር ነበር በቻይናዋ ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው፡፡
ቻይና ኮሮና ቫይረስ የተቀሰቀሰበትን ውሀን ከተማ በቁጥጥር ስር ከደረገች በኋላ ዋነኛው ስጋቷ ከውጭ የሚመጣው በመሆኑ ምክንያት ከውጭ ወደ ሀገሪቱ በሚገቡ የውጭ ዜጎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች ነው፡፡ ቻይና ምንም አይነት ማግለል እያደረገች እንዳልሆነ አስታውቃለች፡፡
በቅርቡ በጓንዙ የሚኖሩ አፍሪካውያን በአከራዮቻቸው ከሚኖሩበት ቤት እንዲወጡና የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በርካታ ጊዜ ቢደረግላቸውም ውጤቱም አይሰጣቸውም፤ በአደባባይ እየተንጓጠጡና እየተገለሉ ይገኛሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ቅሬታ በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚነገር ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአፍሪካ አምባሳደሮች ይህ አይነት መድሎና ማግለል ቫይረሱ በአፍሪካውያን እየተሰራጨ ነው የሚል ውሸት አንደምታ ይፈጥራል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛኦ ሊጂያን በበኩላቸው የጓንዙ ባለስልጣናት ለአፍሪካ ትልቅ ትኩረት ይሠጣሉ፤ ስለሆነም የአፍሪካ ሀገራት ያነሱትን ቅሬታ በፍጥነት እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡
ነገርግን ቃል አቀባዩ ዛኦ በአፍሪካውያን ላይ እየደረሰ ነው ስለሚባው ማግለል ያሉት ነገር የለም፡፡