የአፍሪካና የካሪቢያን ሀገራት ለባርነት ካሳ ለመጠየቅ ትብብር ፈጥረዋል ተባለ
በባርነት ለተፈጸሙ "ታሪካዊ ወንጀሎች" ማካካሻ ያስፈልገዋል ተብሏል
ለባርነት "የአህጉር አቀፍ ዘመቻ" መጀመሩን ተሟጋች ተቋማት ተናግረዋል
በዚህ ሳምንት በቤርባዶስ ዋና ከተማ ብሪጅታውን በተካሄደ ታሪካዊ ዝግጅት ከተለያዩ የአፍሪካ እና የካሪቢያን ሀገራት ተወካዮች ባርነት እና ለዛሬው ማህበረሰብ ላለውን ትሩፋት ካሳ ጠይቀዋል።
የምዕራብ ኢንዲስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የባህል ም/ቤት፣ የቤርባዶስ መንግስት፣ የእርዳታ ሰጭ አውታር ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን እና የካሪቢያን ፓን አፍሪካ ኔትዎርክ "የካሳ ጥሪ" አቅርበዋል።
ድርጅቶቹ ለተፈጸሙ "ታሪካዊ ወንጀሎች" ማካካሻ ያስፈልገዋል ብለዋል።
ለአራት ቀናት የተካሄደው ስብሰባ የስልታዊ ክፍለ ጊዜዎች እና ምልዓተ ጉባኤዎችን ያካተተ ሲሆን ለባርነት "የአህጉር አቀፍ ዘመቻ" መጀመሩን ያመላክታል ሲል መግለጫው ጠቅሷል።
ተሳታፊዎቹ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት እና የካሪቢያን ማህበረሰብ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ህብረት (ካሪኮም) አምባሳደሮች እና ተወካዮች ይገኙበታል ተብሏል።
“ይህ ታሪካዊ ወቅት ነው። የሰው ልጅ በቅኝ ግዛት መርዛማ ጣልቃ-ገብነቶች ወደፊት መሄድ አይችልም" ሲሉ የካሪኮም የካሳ ኮሚሽን ኃላፊ ተናግረዋል።
"የሰው ልጅ እንዲሰራ ይህን ቆሻሻ ማጽዳት አለብን" ሲሉ አክለዋል።
እንደ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ፖርቹጋል ካሉ የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ካሳ ለመጠየቅ የተቋቋመው የካሪኮም የካሳ ኮሚሽን፤ "ባርነት እና የዘር ማጥፋትን ለዛሬ ስቃይ ዋና ምክንያት አድርጎ ይመለከታል"።
የስብሰባው ውጤቶች በአፍሪካ ህብረት እና በካሪኮም መካከል የትብብር ፍኖተ ካርታ ያካትታል ተብሏል።
ባርነት በቅኝ ግዛትና ዘረኝነት ላይ ያለውን ግዙፍ ትስስርና በዓለም ዙሪያ በጥቁር ህዝቦች ላይ ያለውን ተጽዕኖ ማየት አስፈላጊ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ተናግረዋል።
ከ15ተኛው እስከ 19ነኛው ክፍለ ዘመን 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካዊያን በአውሮፓዊያን በግዴታ ተግዘው ለባርነት መሸጣቸው ይታመናል።