የደች ንጉስ ሀገራቸው ለነበራት የባርነት ተሳትሮ ይቅርታ ጠየቁ
ንጉስ የደች የንጉሳውያን ቤተሰቦች በባርነት ጉዳይ የነበራቸውን ትክክለኛ ሚና ለመለየት ጥናት እያስጠኑ መሆናቸውን ገልጸዋል
ባለፈው አመት ሩቴ ይቅርታ ሲጠይቁ፣ የባርያ ንግድ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች ስለሚኖረው ካሳ አልተናገሩም ነበር
የደች ንጉስ ዊለም አሌክሳንደር የባርያ ንግድ የቀረበትን 150ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ባሰሙት ንግግር ሀገራቸው ለነበራት የባርያ ንግድ ተሳትፎ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ንጉሱ ይቅርታም እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።
የንጉሱ ይቅርት ባለፈው አመት የደች ወይም የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ ሀገራቸው ለነበራት የባርያ ንግድ ተሳትፎ ይቅርታ መጠየቃቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።
ንጉስ ዊሊየም ባሰሙት ሰሜታዊ ንግግር " ዛሬ በፊታችሁ ቆሚያለሁ።ዛሬ እንደ መንግስት እና ንጉስ ራሴ ይቅርታ ጠይቂያለሁ። የቃላቱ ክብደት ከልቤ ተሰምቶኛል"ብለዋል።
ንጉስ የደች የንጉሳውያን ቤተሰቦች በባርነት ጉዳይ የነበራቸውን ትክክለኛ ሚና ለመለየት ጥናት እያስጠኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ነገርግን ዛሬ በዚህ በሰብአዊነት ላይ ለተፈጸመው ወንጀል ይቅርታ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ንገሱ።
በአምስተርዳም በሚገኘው የባርያ ንግድ ሰለባውያንን ለማስታወስ በተሰራው ሀውልት የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡት ንጉስ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ሆነው ነበር።
የቀድሞ የህግ ሰው ጆን ሊር ዳም የሆኑት ንጉስ ይቅርታ ሲጠይቁ እንባ እንደተናነቃቸው ይናገራሉ።
ይህ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል ጆን ሊርዳም።
ባርነት በደች ቅኝ ግዛት ስር በነበሩት የካሪቢያን ሀገራት በፈረንጆቹ 1963 በይፋ ቢያበቃም፣ በባርነት ተወስደው የነበሩት ሰዎች ግን ለተጨማሪ 10 አመታት የጉልበት ስራ ሰርተዋል።
ባለፈው አመት ሩቴ ይቅርታ ሲጠይቁ፣ የባርያ ንግድ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች ስለሚኖረው ካሳ አልተናገሩም ነበር።
በምትኩ የደች መንግስት በኔዘርላንድና በቀድሞ የደች ቅኝ ግዛት ሀገራት የባርያ ንግድ አይነት ተግባራትን ለማስቀረት 217 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን መግለጹ ይታወሳል።