50 ሚሊዮን ዜጎቻቸውን በባርነት የሚያኖሩ ሀገራት እነማን ናቸው?
22 ሚሊዮን የዓለማችን ዜጎች በግዳጅ ጋብቻ ውስጥ እንደሚኖሩ ተገለጸ
በአሁኑ ወቅት 50 ሚሊዮን የዓለማችን ዜጎች በባርነት ውስጥ እንደሚኖሩ አንድ ጥናት አመልክቷ
50 ሚሊዮን ዜጎቻቸውን በባርነት የሚያኖሩ ሀገራት እነማን ናቸው?
የባሪያ ንግድ ከቆመ አልያም እንዲቆም ከተወሰነ ከ150 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ባርነት መልኩን ቀይሮ ዜጎችን ለስቃይ እየዳረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ኤኤፍፒ ወክ ፍሪ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም ያስጠናውን ጥናት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ አሁን ላይ 50 ሚሊዮን ዜጎች በዘመናዊ ባርነት ውስጥ እየኖሩ ናቸው፡፡
በባርነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጸው ይሄው ጥናት ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በቻ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ዜጎች ወደ ባርነት ህይወት ገብተዋል ተብሏል፡፡
ጦርነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የጤና ወርርሽኞች መስፋፋት በባርነት የሚኖሩ ዜጎችን ቁጥር እየጨመረው እንደሆነም በጥናቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
በነዚህ ጉዳቶች ምክንያትም ተገደው ወደ ትዳር የሚገቡ ዜጎች ቁጥር መጨመር፣ ወደ ወሲብ ንግድ መግባት፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና ሌሎችም የግዳጅ ህይወቶች በዜጎች ላይ እየተጫኑ ነውም ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅትም 28 ሚሊዮን ዜጎች በግዳጅ ስራ ውስጥ ያሉ ሲሆን 22 ሚሊዮን ያህል የዓለማችን ዜጎች ደግሞ በግዳጅ ትዳር ውስጥ ህይወታቸውን እየመሩ እንደሆኑ ይሄው ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በዓለማችን ከ150 ዜጎች መካከልም አንድ ሰው በባርነት ህይወት ውስጥ እየኖሩ እንደሆነ ሲገለጽ የቡድን 20 አባል ሀገራት ሳይቀር ዜጎች የባርነት ህይወት እንዲመሩ እያደረጉ ናቸው ተብሏል፡፡
ሰሜን ኮሪያ፣ ኤርትራ፣ ሞሪታኒያ ከፍተኛ መጠን ያለው ህዝባቸው በባርነት እንዲኖር ያደረጉ ሀገራት ተብለዋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ኩዌት በባርነት የሚኖሩ ሰዎች ያሉባቸው ተጨማሪ የዓለማችን ሀገራት እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ሕንድ፣ ቻይና እና ሩሲያም ከአምስት ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ያል ህዝባቸውን በባርነት ውስጥ እንዲኖሩ ያደረጉ ሀገራት ናቸውም ተብሏል፡፡