የአፍሪካ ምግብ ዋስትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ
19ኛው የአፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል
በጉባኤው ላይ የኮፕ28 ፕሬዝዳንት ዶክተር ሱልጣን ጃቢር እና የአፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ተገኝተዋል
የአፍሪካ ምግብ ዋስትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ።
19ኛው የአፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ጉባኤ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት እድሎችን መጠቀም እና ትብብርን ማጎልበት" በሚል ሀሳብ በአዲስ አቡባ ተካሂዷል።
በዚህ ጉባኤ ላይ አፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች፣ የዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓመታዊ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አዘጋጅ ሀገር ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር ተገኝተዋል።
እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ተቋማት መሪዎች እንደተገኙ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካን የምግብ ዋስትና እየፈተነ ነው ብለዋል።
አቶ ደመቀ አክለውም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን ለመከላከል እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ አረንጓዴ አሻራ ስትራቴጂ ነድፋ እየተገበረች መሆኗንም ጠቅሰዋል።
የኮፕ28 አለም አቀፍ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር በበኩላቸው አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ እየተጎዱ ካሉ አህጉራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶክተር አል ጃቢር አክለውም የፊታችን ህዳር በዱባይ የሚካሄደው ኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለአፍሪካ እና ለቀሪ አህጉራት የሚጠቅም ውሳኔ የሚተላለፍበት እንደሚሆንም አክለዋል።
አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሰባት ላለው ጉዳት የገንዘብ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑንም ዶክተር አልጃቢር በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አሳስበዋል።