ፑቲን የህገመንግስት ማሻሻያ ምርጫው መራዘሙን አስታወቁ
ማሻሻያው ፑቲን እ.ኤ.አ ከ2024 በኋላ ለሁለት ዙር እንዲመሩ ያሚያስችላቸው አንቀጽ እንዳካተተ ተነግሯል
ሚያዚያ 14፤2012 ዓ.ም እንዲካሄድ ጊዜ ተይዞለት የነበረው የሩሲያ የህገመንግስት ማሻሻያ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ
ሚያዚያ 14፤2012 ዓ.ም እንዲካሄድ ጊዜ ተይዞለት የነበረው የሩሲያ የህገመንግስት ማሻሻያ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ
የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቪላድሚር ፑቲን ለሚያዚያ 14፤2012 ዓ.ም እንዲካሄድ ጊዜ ተይዞለት የነበረው የሩሲያ የህገመንግስት ማሻሻያ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደሚራዘም አስታወቁ፡፡
እስከዛሬ ድረስ በተጠናቀረው መረጃ መሰረት በሩሲያ እስካሁን 658 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡ፑቲን ለምርጫው አዲስ ቀን አላስቀመጡም፤ ምክንያታቸው ደግሞ አዲሱ የሚካሄድበት ቀን በኮሮና ቫይረስ ሁኔታ ስለሚወሰን ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዘዳንት ፑቲን ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ የህገመንግስታዊ ማሻሻያ ረቂቅ አዘጋጅተው ነበር፤ ማሻሻያው ፕሬዘዳንት እ.ኤ.አ ከ2024 በኋላ ለሁለት ዙር እንዲመሩ ያሚያስችላቸው አንቀጽ እንዳካተተ ተነግሯል፡፡
ለፓርላማውና ለፕሬዘዳንቱ ተጨማሪ ስልጣን በመስጠት ማሻሻያው የኃይል ሚዛን ይቀይራል ተብሏል፡፡
መጀመሪያ ጤና መቅደም አለበት ያሉት ፕሬዘዳንቱ በቴሌዥን ባስተላለፉት መልእክት አስፋላጊ ከሆኑት ዘርፎች በስተቀር ሩሲያዉያን ቤታቸውን ዘግተው እንዲቀመጡ ማዘዛቸው ይታወሳል፡፡