ፖለቲካ
በርካታ እስረኞች የሚገኙባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በአፍሪካ የእስረኞች ቁጥር ከ2020 ወዲህ በ53 በመቶ ጨምሮ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ደርሷል
በወርልድ ፕሪዝን ፖፑሌሽን መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ከ110 ሺህ በላይ ሰዎች በእስር ላይ ይገኛሉ
የመንግስታቱ ድርጅት ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 140ዎቹ በማረሚያ ቤቶች እንደሚገኙ ይገልፃል።
በአለማቀፍ ደረጃ በአሁኑ ወቅት 11 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡
ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 4 ሚሊየኑ በአፍሪካ ውስጥ እንደሚገኙ የወርልድ ፕሪዝን ፖፑሌሽን መረጃ ያሳያል።
ከቻይና እና ደቡብ ኮሪያ ውጭ በአለማቀፍ ደረጃ የ223 የማረሚያ ቤቶች የያዟቸውን እስረኞች ቁጥር በየጊዜው ይፋ የሚያደርገው ወርልድ ፕሪዝን ፖፑሌሽን፤ በአፍሪካ የእስረኞች ቁጥር ከ2020 ወዲህ በ53 በመቶ መጨመሩን አመላክቷል።
በምዕራብ አፍሪካ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ምጣኔ ከ100 ሺህ 50 ሲሆን፤ በደብብ አፍሪካ ሀገራት ደግሞ ወደ 243 ከፍ ይላል።
በአህጉሪቱ በርካታ ዜጎችን በማሰር ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ግብፅ ትከተላለች። ወርልድ ፕሪዝን ፖፑሌሽን 110 ሺህ ሰዎችን በማረሚያ ቤቶች ይዛለች ያላት ኢትዮጵያ ደግሞ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ሩዋንዳ ከ1994ቱ የዘር ፍጅት ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎችን በማሰር ቀዳሚ ሆና የቆየች ቢሆንም ከ2000 ጀምሮ ታራሚዎችን እየፈታች በመሆኑ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።