ለእስረኞች በድብቅ አልኮል የሚሰጠው ከንቲባ
ከንቲባው በመጨረሻም ድርጊቱ ታውቆበት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል
የከተማዋ ከንቲባ ከእስር በዋስ ቢለቀቅም ከስራው እንደታገደ ነው
ለእስረኞች በድብቅ አልኮል የሚሰጠው ከንቲባ
በመላው ዓለም በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብለው በማረሚያ ቤት ውስጥ ላሉ እስረኞች ከሚከለከሉ ነገሮች አንዱ አልኮል ነው።
ቤንጃሚን ክራንፎርድ የጆርጂያዋ ቶምፕሰን ከተማ ከንቲባ ሲሆን ከሰሞኑ ያደሩገው ክስተት አነጋጋሪ ሆኗል።
ይህ የከተማዋ አስተዳዳሪ በከተማዋ ባለ እስር ቤት ላሉ እስረኞች አልኮል አስገብቷል ተብሏል።
ፖሊስ እንዳስታወቀው ከሆነ የከተማዋ ከንቲባ ለእስረኞች አልኮል ሲያስገቡ እንደነበር እና ህግ ተላልፈው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
ፖሊስ አክሎም ከንቲባው በህግ ከተሰጣቸው ሀላፊነት ውጭ ያልተፈቀደላቸውን ስራ ሲሰሩ ተድርሶባቸዋል ብሏል።
ይህን ተከትሎ ጉዳዩ የበርካቶች መነጋገሪያ ሲሆን ከንቲባው ለምን አልኮል እንዳስገቡ እስካሁን አልተናገሩም።
የፖሊስን ምርመራ ተከትሎ ከንቲባው ከሀላፊነት የታገዱ ሲሆን የተመሰረተባቸው ክስ እልባት ሳያገኝ ወደ ስራ አይመለስም ተብሏል።
ደረቅ ጅን ለእስረኞች አስገብተዋል የተባሉት የ52 ዓመቱ ከንቲባው ከአንድ ዓመት በፊት ነበር በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡት።
ፓርቲያቸው ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ክስ የተመሰረተባቸው የከተማው ከንቲባ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ከተባሉ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።