የግብጽ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ አፈጻጸም ለህዝብ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍለት ጠየቀ
የ22 ዓመት ግብጻዊ ከአንድ ወር በፊት የፍቅር ጥያቄዬን አልተቀበልሽም በሚል ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔት መግደሉ ይታወሳል
የግብጽ ፍርድ ቤትም በዚህ ገዳይ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ አስተላልፏል
በግብጽ ያለ አንድ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ አፈጻጸም ለህዝብ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍ ጠይቋል።
በግብፅ ከአንድ ወር በፊት መሀመድ አደል የተሰኘ አንድ ግለሰብ የፍቅር ጥያቄዬን አልተቀበልሽም በሚል ናይራ አሽራፍ የተባለች እንስት በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ወግቶ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ በርካቶችን አስቆጥቷል፡፡
ግለሰቡ ይህችን እንስት ከምትማርበት ዩንቩርሲቲ መግቢያ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ወግቶ መግደሉ በግብጽ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ፖሊስ ተጠርጣሪውን ወዲያው በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን አጠናቆ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቷል።
ፍርድ ቤቱም በ21 ዓመቱ ተጠርጣሪው ላይ የሞት ፍርድ ያስተላለፈ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የሞት ፍርድ ውሳኔ አፈጻጸሙ ለህዝብ በቀትታ እንዲተላለፍ ጠይቋል።
ግብጽ እስካሁን የሞት ፍርድ አፈጻጸሞችን ለህዝብ በቀትታ አስተላልፋ የማታውቅ ሲሆን ይህ ግድያ ግን ህዝብን እንዲያስተምር በማሰብ የሞት ፍርድ አፈጻጸሙ በቴሌቪዥን በቀትታ እንዲተላለፍ ፍርድ ቤቱ የሀገሪቱን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በደብዳቤ ጠይቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በግብጽ የሴቶች ጥቃት በስፋት እንደሚፈጸም የሚገለጽ ሲሆን ተመድ በ2015 አካሄድኩት ባለው ጥናት ስምንት ሚሊዮን ግብጻውያን ሴቶች ጥቃቶችን አስተናግደዋል