ሰሜን ኮሪያ፣ የደቡብ ኮሪያን ፊልም አስተዋውቀዋል ያለቻቸውን ታዳጊዎች በሞት ቀጣች
የደቡብ ኮሪያን ፊልሞች ሲያከፋፈል እና ሲሸጥ የተያዘ በሞት ይቀጣል
በሞት የተቀጡት ሁለቱ ወጣቶች ፈልም የያዘ ሲዲ ሊሸጡ ሞክረዋል ተብሏል
የሰሜን ኮሪያ መንግስት የደቡብ ኮሪያ ፊልም አስተዋውቀዋል ያላቸውን ሁለት ታዳጊዎች በሞት መቅጣቷ ተገልጿል፡፡
የእንግሊዙ ዴይሊ ኤክስፕረስ ጋዜጣ እንደዘገበው የአካባቢው ነዋሪዎች ከተፈረደባቸው በኋላ የ16 እና 17 አመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎች ሲገደሉ በግዳጅ እንዲያዩ ተደርገዋል፡፡
እንደዘባው ከሆኑ የሞት ቅጣቱ የተከወነው ባፈው ጥቅምት ወር ቢሆንም ግድያውን የሚያሳይ መረጃ የወጣው ግን ባለፈው ሳምንት ነው፡፡
ሌላም ታዳጊ የእንጀራ እናቱን በመግደሉ በሞት የተቀጣ ሲሆን ባለስልጣናቱ ወንጀሉ እኩል ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል፡፡ ግድያውን እንዲያዩ የተገደዱ ነዋሪዎች የግድያውን ዘግናኝነት መናገራቻን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡
በሞት የተቀጡት ሁለቱ ወጣቶች ፈልም የያዘ ሲዲ ሊሸጡ ሞክረዋል ተብሏል፡፡ የሰሜን ኮሪያ መንግስት እነዚህን የሚሸጡ ሰዎችን የሚጠቁም ሰው በህዝኑ ውስጥ በማሰራጨቱ ምክንያት ታዳጊዎች ወጥመድ ውስጥ ሊገቡ ችለዋል፡፡
የምእራባውያን እና የደቡብ ኮሪያ ፊልሞች እና ሙዚቃዎች ወደ ሰሜን ኮሪያ ቻይና በኩል የሚገቡት ቡዩኤስቡ እና በፍላሽ አማክኝነት ነው፡፡ ሰሜን ኮሪያ፣ የደቡብ ኮሪያ ፊልሞች በግዛቷ የሚታዩ ከሆነ በወጣቱ ትውድል ላይ ተጽእኖ ሊፈጥሩ ይላሉ የሚል ስጋት አላት፡፡
በሰሜን ኮሪያ፣ የደቡብ ኮሪያ ፊልም ማሳየት የሚያስቀጣና የሚያሰድድ መሆኑንም ተዘግቧል፡፡ ነገርግን የደቡብ ኮሪያን ፊልሞች ሲያከፋፈል እና ሲሸጥ የተያዘ በሞት ይቀጣል፡፡