ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ አባል ሀገራት ሽልማት አሸነፈ
አየር መንገዱ የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ አሸናፊ ሆኗል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” ነው የተቀበለው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ አሸናፊ ሆነ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ በሚከናወነው የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው የተሸለመው።
በዚህም አየር መንገዱ ዓመታዊውን የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” አሸናፊ ሆኗል።
ሽልማቱ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ለሚኖረው የንግድ ትስስር፣ የአፈፃፀም ልህቀት እና ፈጠራ ዕውቅና የሚሰጥ ተብሏል።
የብሪክስ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በአባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ የንግድና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎችን ለማበረታታት እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ምክር ቤት መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።