በውጊያ አውሮፕላኖች ብዛት ቀዳሚ ሀገራት (2024)
ከ1911 ጀምሮ በጦርነት ውስጥ መሳተፍ የጀመሩ አውሮፕላኖች ከቅኝት እስከ ቦምብ መወርወር በጦርነቶች ላይ አይነተኛ ሚና አላቸው
ሀገራት የበርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖች ባለቤት ለመሆን የሚያደርጉት ፉክክር በድሮን መምጣትም ሊቀንስ አልቻለም ተብሏል
አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ ለጦርነት የዋለው በፈረንጆቹ 1911 ነው።
ጣሊያን በኦቶማን ኢምፓየር ስር የነበረችውን ሊቢያን ስትወር አውሮፕላኖችን በመጠቀም የቱርክን ወታደራዊ መረጃዎች መቃኘት መቻሏን የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ።
ጣሊያን የጀመረችውን አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ሶቪየት ህብረትና ሌሎችም ሀገራት በሁለቱም የአለም ጦርነቶች ወቅት እንዳስቀጠሉትም ይወሳል።
ወታደሮች የሚገኙበትን ስፍራ ለመቃኘትና ምስል በማንሳት የጀመረው የውጊያ አውሮፕላኖች ሚና በየጊዜው እያደገና እየዘመነ ቦምብ ታጥቆ ከተሞችን እስከማደባየት ድረስ ዘልቋል።
ሀገራት በስአት ከ1 ሺህ 600 ኪሎሜትር በላይ የሚምዘገዘጉ፤ እንዳሻቸው የሚገለባበጡ፣ አየር በአየር ሚሳኤል የሚተኩሱና አውሮፕላን የሚጥሉ የውጊያ አውሮፕላኖችን ለመስራት ችለዋል።
በውጊያ አውሮፕላን የበላይነት ለመያዝ የሚደረገው ጥረት በድሮን መምጣት ይደበዝዛል ተብሎ ቢጠበቅም ከፍተኛ ክብደት ያላቸውን ቦምቦች እና ሚሳኤሎች የሚሸከሙ አውሮፕላኖች ተፈላጊነት እየጨመረ መሄዱን የግሎባል ፋየርፓወር መረጃ ያሳያል።
በሶቪየት ህብረት ዘመን በ1970 ስራ የጀመረው “ሚግ-25” እና 46ኛ አመቱን የያዘው የአሜሪካው “ኤፍ- 16” የውጊያ አውሮፕላኖች በዘመን ብዛት ተፈላጊነታቸው አለመቀነሱንም በመጥቀስ።
በግሎባል ፋየርፓወር መሰረት በርካታ የውጊያ አውሮፕላኖች ያሏቸውን 10 ሀገራት ይመልከቱ፦