በአፍሪካ ናይጄሪያ 24 ሚሊየን የጎዳና ተዳዳሪዎች መገኛ በመሆን ቀዳሚዋ ናት
በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች መኖርያቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎች ቁጥር በአለም አቀፍ ደረጃ 140 ሚሊየንን ተሻግሯል፡፡
የከተሞች መስፋፋት እና ስራ አጥነት፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የኑሮ ውድነት እና ድህነት ሰዎች ወደ ጎዳና እንዲወጡ ከሚያስገድዱ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
በተጨማሪም በፖለቲካዊ ምክንያቶች ለዚህ ችግር የሚዳረጉ ዜጎች ቁጥርም ቀላል እንዳልሆነ ይነገራል፡፡
ናይጄሪያ 24 ሚሊየን የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመያዝ ቀዳሚዋ ስትሆን ግብጽ በ12 ሚልየን ትከተላታለች።
በሚልየን የሚቆጠሩ ጎዳና ተዳዳሪዎች ያሉባቸው ሀገራት እንዳሉ ሁሉ አንድም የጎዳና ተዳዳሪ የሌለባቸው ጥቂት ሀገራትንም መጥቀስ ይቻላል፡፡
ጆርዳን፣ ቡታን፣እና ቫቲካን ሲቲ ከነዚህ መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በአፍሪካ ከፍተኛ የጎዳና ተዳዳሪ ቁጥር ያለባቸው 10 ሀገራት የትኞቹ ናቸው? ይመልከቱ።