ላለፉት 4 ቀናት በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ፋሽን ሾው ተጠናቀቀ
የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ በአፍሪካ ከግብርና በመቀጠል ከፍተኛው የስራ እድል የሚፈጥር ዘርፍ ነው
በፋሽን ሾው ላይ ከ27 አገራት የመጡ አፍሪካዊያን ዲዛይነሮች ተሳትፈዋል
በአዲስ አበባ ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአፍሪካ ፋሽን ሾው ተጠናቀቀ።
ፋሽን ሾው በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት ነበር ላለፉት አራት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል ሲካሄድ የነበረው።
በፋሽን ትዕይንቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ27 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ በጨርቃጨርቅ ምርት እና ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ከ800 በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል።
የትዕይንቱ ዋና አላማ የአፍሪካውያንን አንድነት ማጠናከር ሲሆን በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች እና ነጋዴዎች መካከል ትስስር ለመፍጠር እንደነበር አል ዐይን ኒውስ የሾዉ አዘጋጅ ከሆኑት ሌክሲ ሙጎ ሰምቷል።
እንዲሁም አፍሪካውያን ዲዛይነሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ ተመሳሳይ ትዕይንቶች ላይ እንዲሳተፉ እድል ለመፍጠር ሌላኛው የዚህ ትዕይንት ዓላማ መሆኑ ተገልጿል።
አፍሪካ እምቅ የጨርቃጨርቅ ምርት አቅም ቢኖራትም አሁንም አብዛኛው አፍሪካዊ አልባሳትን ከበለጸጉ አገራት በከፍተኛ ውጭ ምንዛሬ እያስገቡ ነው የሚለው ሌክሲ ይሄንን ለመቀየር እና አፍሪካዊ ሸማኔዎችን ማበረታታት አለብን የዛሬው የፋሽን ሾው አላማም የገበያ ትስስር፣ የቴክኒሎጂ እና የእውቀት ልምዶችን እንዲለዋወጡ ማድረግ ነው ብሏል።
የደቡብ አፍሪካ ዲዛይነሮችን በመወከል በዚህ በፋሽን ሾው ላይ የተሳተፈው ዲዛይነር ንጎጺ ናቲ ያሶ በበኩሉ በአፍሪካዊ አለባበስ ዘይቤ ለአፍሪካዊያን አልባሳትን ማዘጋጀት አለብን እንደዚህ አይነት መድረኮችም ከደቡብ አፍሪካ ውጪ ያሉ አዳዲስ ደንበኞችን እንድተዋወቅ ረድቶኛል ብሏል።
አፍሪካውያን በ2022 የአህጉሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ሊሰሩ እንደሚገባ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር አሳሰቡ
እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ ሪፖርት ከሆነ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ በአፍሪካ ለዜጎች የስራ እድሎችን በመፍጠር ከግብርና ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።