የዱባይ ኤክስፖ 2020 የኢትዮጵያ እልፍኝ /ፓቪሊዮን/ በትናትናው እለት በይፋ ተከፍቷል
ኢትዮጵያ በዱባይ ኤክስፖ የኢንቨስትመንት አማራጮቿን፣ ንግድና ቱሪዝም እድሎቿን ለማስተዋወቅ ስትሰራ የቆየች ሲሆን፤ ሀገሪቱን ለማስተዋወቅ ይበጁኛል ያለቻውን በሙሉ ወደ ስፍራው ይዛ ተጉዛለች።
- ኢትዮጵያ በዱባይ 2020 ኤክስፖ ምን ይዛ ቀርባለች…?
- በዱባይ ኤክስፖ የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት፣ንግድና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ እየተሰራ ነው-ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
ሉሲ ድንቅነሽ በኤክስፖ 2020 ዱባይ ላይ ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ቀደም ብላ ዱባይ የገባች ሲሆን፤ በኤክስፖው ሉሲ ለ6 ወራት ለጎብኚዎች ለእይታ ቀርባለች። ሉሲም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም ማህበረሰብ በኤክስፓው ለእይታ ቀርባለች።
ከሉሲ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ታሪክ እና ባህል የሚያሳዩ የተለያዩ ቁሳቁሶች በተንቀሳቃሽ ምስል ተደግፈው ለጎብኚዎች የሚቀርቡ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ቡና በኤክስፖው ላይ ከሚቀርቡት ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የቡና ምርት ታሪክ፣ የቡና አመራረት ሂደት እና የቡና ፍሬ ለእይታ የሚቀርብ ይሆናል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የቡና ባህላዊ የቡና ማፍላት ስነ ስርዓት በኤክስፖው ላይ ለጎብኚዎች የሚቀርብ ይሆናል።
የዱባይ ኤክስፖ 2020 ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 192 ሀገራት እንደሚሳተፉበት የሚጠበቅ ሲሆን፤ ከ25 ሚልየን በላይ ጎብኚዎች እንደሚጎበኙበትም ይጠበቃል።
የዱባይ 2020 ኤክስፖ ከጥቅምት እስከ መጋቢት 2013 ዓ.ም ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም፤ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ መራዘሙም ይታወሳል።
በአረብ ሀገራት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚካሄድ ለተነገረለት የዱባይ ኤክስፖ 2020 ከ10 ዓመት በላይ የፈጀ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።