በሩሲያ የእህልና የማዳበሪያ ምርት ላይ የሚያጋጥሙ መሰናክሎች ካልተወገዱ የጥቁር ብህር ስምምነት ይቋረጣል አለች
ተመድ የጥቁር ባህር እህል ስምምነትን ለማዳን እየሞከረ ነው
ስምምነቱን በማስፋት ተጨማሪ የዩክሬን ወደቦችን እና ሌሎች ጭነቶችን ለማካተት ውይይት እንደሚደረግ ተነግሯል
በሩሲያ የእህልና የማዳበሪያ ምርት ላይ የሚያጋጥሙትን መሰናክሎች ካልተወገዱ ስምምነቱ ይቋረጣል ስትል አስጠንቅቃለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ኪየቭ፣ ሞስኮ እና አንካራ የሩሲያን ማዳበሪያ በዩክሬን በኩል ለማጓጓዝ የዝግጅት ስራ እንዲጀምሩ ሀሳብ አቅርቧል።
ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደተናገሩት ከዩክሬን ደህንነቱ የተጠበቀ እህልን ወደ ውጭ ለመላክ የጥቁር ባህር እህል ስምምነትን ለማዳን እየተሞከረ ነው።
የዝግጅት ስራው ሲጀመር ተመድ ባለፈው ሀምሌ ወር የተደረሰውን የጥቁር ባህር ስምምነትን በማስፋት ተጨማሪ የዩክሬን ወደቦችን እና ሌሎች ጭነቶችን ለማካተት ውይይት እንዲደረግ ይፈልጋል ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሮይተርስ ምንጭ ተናግረዋል
ሩሲያ በዚህ ወር ስምምነቱ ለሁለት ወራት እንዲራዘም ተስማምታለች። ነገር ግን በሩሲያ የእህል እና የማዳበሪያ ምርት ላይ የሚያጋጥሙትን መሰናክሎች ለማስወገድ የሚያስችል ስምምነት እስካልተሟላ ድረስ ውጥኑ ይቋረጣል ብላለች
ዩክሬን እና ቱርክ በጥቁር ባህር እህል ስምምነት ለማሻሻል የታቀደውን አዲሱን ሀሳብ ተቀብለው ቢስማሙም ሩሲያ ግን እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም ሲል ምንጩ ገልጸዋል።
የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪች ንግግሮች እንደቀጠሉ ተናግረዋል።
"ዋና ጸሐፊው የጋራ ማስተባበሪያ ማዕከልን ሥራ ለማመቻቸትና ለማሻሻል፣ የተፈረመው ስምምነት አካል በሆነው የማዳበሪያ (አሞኒያ) ጉዳይ ላይ ለመስራት አንዳንድ ሀሳቦችን ለሀገራቱ አቅርበው ነበር። ንግግሮች እና ግንኙነቶች እየቀጠሉ ነው። ግን አሁን የምናገረውን ይህን ነው" ብለዋል።
ተመድ እና ቱርክ ባለፈው ሀምሌ ዓለም አቀፍ የምግብ ችግር ለመቅረፍ እንዲረዳ በኬየቭና ሞስኮ መካከል ስምምነት እንዲደረስ አደራድረዋል።