ቱርክ በጥቁር ባህር 710 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር መጠን ያለው ጋዝ አገኘች
ፕሬዝደንቱ ኤርዶጋን 58 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ጋዝ ክምችት ሳይኩማ1 በተባለ ቦታ መገኘቱን ተናግረዋል
ቱርክ የተፈጥሮ ጋዝ ለመፈለግ በምታደገው ጥረት በሳካሪያ 13 ቦታዎች ላይ ቁፋሮ ማካሄዷን ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ተናግረዋል
በቱርክ አዲስ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያለበት ቦታ መገኘቱን ተከትሎ በጥቁር ባህር ዳርቻ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት 710 ቢሊዮን ኩቢክ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ መገኘቱን ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ ካቢኔያቸውን በሰበሰቡበት ወቅት 58 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ሳይኩማ1 በተባለ ቦታ መገኘቱን መናራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝደንቱ እንዳሉት አዲስ የተገኘው ክምችት ቀደም ሲል ሳካሪያ በተባለው ቦታ ከተገኘው 652 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር መጠን ካለው ጋዝ ተጨማሪ ነው ብለዋል፡፡
ቱርክ የተፈጥሮ ጋዝ ለመፈለግ በምታደገው ጥረት በሳካሪያ 13 ቦታዎች ላይ ቁፋሮ ማካሄዷን ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ተናግረዋል፡፡
ኤርዶጋን እንደተናሩት በሳይኩማ 1 በተገኘው የጋዝ ክምችት ምክንያት ቱርክ በአጠቃላይ በጥቁር ባህር ያላት የጋዝ ክምችት ወደ 710 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ከፍ ብሏል፡፡