በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዋና ከተሞች
ከ5.2 ሚሊየን በላይ ነዋሪ ያላት አዲስ አበባ በነዋሪዎች ብዛት ከአፍሪካ 5ኛ ከአለም ደግሞ 32ኛ ደረጃን ይዛለች
በግሎባል ፋየርፓወር ሪፖርት መሰረት የግብጽ መዲና ካይሮ በአፍሪካ በርካታ ህዝብ የሚኖርባት ከተማ ናት
የአለማችን መጻኢ የሚወሰነው በፈጣን የህዝብ እድገት ባለችው አፍሪካ እንደሆነ ይነገራል።
በህዝብ ብዛት ከእስያ የምትከተለው አፍሪካ እንደ ቻይና እና ጃፓን ያሉ ሀገራት የውልደት መጠን ማነስ ሲያሳስባቸው የህዝብ ቁጥሯ በፍጥነት እያደገ ነው።
የአህጉሪቱ ፈጣን የህዝብ እድገት ለስራ ብቁ የሆነ ወጣት የሰው ሃይል እድል ይዞ የመምጣቱን ያህል ግን በከተሞች ላይ ጫናው እየጨመረ መሄዱ ተደጋግሞ ይነሳል።
ከተሞች የፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ማዕከል መሆናቸው ከገጠራማ ስፍራዎች የሚፈልሰውን ስራ ፈላጊ ዜጋ ቁጥር እያሳደገው በተቀባዮቹ ከተሞች ላይ ጫና ማሳደሩ አልቀረም።
በተለይ ወደ ዋና ከተሞች የሚደረገው ፍልሰት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን የሚያነሳው የግሎባል ፋየርፓወር ሪፖርት በ2024 በርካታ ነዋሪዎች ያሏቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት መዲናዎችን ይፋ አድርጓል።
በሪፖርቱ መሰረት የግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በአፍሪካ በርካታ ህዝብ የሚኖርባት ከተማ ናት።
ከ5 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ነዋሪ ያላት አዲስ አበባ ደግሞ ከአፍሪካ በ5ኛ ከአለም ደግሞ በ32ኛ ደረጃ ተቀምጣለች።