ብዙ ህዝብ የሚኖርባቸው የዓለማችን ከተሞች እነማን ናቸው?
የእስያ ሀገራት ከተሞች በህዝብ ብዛት የተጨናነቁ ናቸው ተብሏል
ከአፍሪካ የግብጽ ካይሮ እና የናይጀሪያዋ ሌጎስ በአንጻራዊነት ብዙ ህዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች ናቸው
ህዝብ የሚኖርባቸው የዓለማችን ከተሞች እነማን ናቸው?
እንደ ዓለም አቀፉ ህዝብ ብዛት ጥናት ተቋም መረጃ ከሆነ የጃፓኗ ቶኪዮ 37 ሚሊዮን ህዝብ በመያዝ የመጀመሪያዋ ብዙ ህዝብ የሚኖርባት ከተማ ተብላለች፡፡
የሕንድ መዲና ዴልሂ 34 በሚሊዮን እንዲሁም የቻይናዋ ሻንጋይ ከተማ ደግሞ በ30 ሚሊዮን ህዝብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ብዙ ህዝብ የሚበዛባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
ቤጂንግ፣ ሜክሲኮ ሲቲ፣ ሞምባይ እና ኦሳካ በተጨማሪነት ከፍተኛ ህዝብ ከሚኖርባቸው ከተሞች መካከል እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
ከአፍሪካ የግብጽ መዲና ካይሮ እና የናይጀሪያዋ ሌጎስ ከተሞች ብዙ ህዝብ ከሚበዛባቸው ከተሞች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡