“ስዋሂሊ” የአፍሪካ ህብረት ተጨማሪ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ተወሰነ
ስዋሂሊ በአፍሪካ ከ100 ሚልየን በላይ ተናጋሪዎች እንዳሉት መረጃዎች ያሳያሉ
ዩኔስኮ፡ ጁላይ 7 የአለም የስዋሂሊ ቋንቋ ቀን ብሎ ማወጁ ይታወቃል
የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስዋሂሊ ቋንቋ ተጨማሪ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወሰኑ።
መሪዎቹ ውሰኔው ያሳለፉት ላለፉት ቀናት በአህጉሪቱ መዲና አዲስ አበባ በተካሄደው 35ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ መሆኑም ታውቋል።
መሪዎቹ ከውሳኔው ላላ የደረሱት የታንዛንያው ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፊሊፕ ምፓንጎ ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ የስዋሂሊ ቋንቋ በአፍሪካ ከ100 ሚልየን በላይ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ መሆኑን በ35ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለተሳተፉ መሪዎች ገልጸዋል።
35ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ የሀገራት መሪዎችም ስሃዋሂሊ ቋንቋን 5ኛ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወስነዋል።
የአፍሪካ ህብረት እስካሁን አረብኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረነሳይኛ፣ ፖርቹጋል እና ስፓኒሽ ቋንቋዎችን የስራ ቋንቋ አድርጎ በመጠቀም ላይ ይገኛል።
"ስዋሂሊ በምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ፣ በደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳዲሲ) እንዲሁም በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የማስተማሪያ ቋንቋን ጨምሮ በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑንም ዶ/ር ፊሊፕ ምፓንጎ አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጁላይ 7 የአለም የስዋሂሊ ቋንቋ ቀን ብሎ ማወጁ ይታወሳል።