ደቡብ አፍሪካ እና ቦትስዋና እስራኤል በህብረቱ የታዛቢነት ቦታ ሊኖራት አይገባም ሲሉ መቃወማቸው ይታወሳል
እስራኤል በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ የታዛቢነት ቦታ ማግኘትን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት አዲስ ኮሚቴ ማቋቋሙን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ፡፡
ምንጮቹ ለአል ዐይን አማርኛ እንዳሉት እስራኤል በአፍሪካ ሕብረት የታዛቢነት ቦታን ለመወሰን የሚያስችል አዲስ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
እንደ ምንጮቹ ገለጻ ስድስት የአፍሪካ ሀገራት ያሉበት ኮሚቴ ለእስራኤል በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ የታዛቢነት ቦታ ይፈቀድ ወይስ አይፈቀድ የሚለውን ጉዳይ ያያል ተብሏል፡፡
ደቡብ አፍሪካ እና ቦትስዋናን ጨምሮ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት እስራኤል በህብረቱ የታዛቢነት ቦታ ሊኖራት አይገባም ሲል መቃወማቸው ይታወሳል፡፡
ጀሬሳሌም ፖስት የሰተኘው የእስራኤሉ ጋዜጣ እስራኤል በአፍሪካ ህብረት ያለት የታዛቢነት ቦታ በተመለከተ በድጋሚ ለመመርመር በህብረቱ የተያዘው አጀንዳ ለሚቀጥለው በቅሚቀጥለው አመት እንዲታይ መወሰኑን ዘግቧል፡፡
ደቡብ አፍሪካና አልጀሪያ፣ እስራኤልን ከህብረቱ የማስወጣት ሙከራቸው መክሸፉን ጋዜጣው ገልጿል፡፡
ትናንትና በተጀመረው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ፤ እስራኤል በሕብረቱ የታዛቢነት ሚና ማግኘት እንደሌለበት ፍልስጤም በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩል ተቃውማለች፡፡ ከፍልስጤም በተጨማሪም ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በአፍሪካ ህብረት የታዛቢነት ቦታ ሊሰጣት እንደማይገባ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
እስራኤል አፍሪካ ሕብረት የታዛቢነት ቦታ ማግኘቷን ተከትሎ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ከፈረንጆቹ 2002 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕብረቱ የእስራኤል ታዛቢ ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡
ይሁንና ይህ የታዛቢነት ጉዳይ በሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ መጽደቅ ነበረበት፡፡ አሁን ላይ አጀንዳው ለ35 ኛው የመሪዎች ጉባዔ ቢቀርብም መሪዎቹ ከመወሰን ይልቅ በኮሚቴ እንዲታይና የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብ ተደርጓል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ቴላቪቭ በአዲስ አበባው መስሪያ ቤት የታዛቢነት ቦታ ማግኘታቸውን ተከትሎ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንብር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡
የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ በበኩላቸው ሀገራቸው በአዲስ አበባው ተቋም የታዛቢነት ቦታ ማግኘቷ ከአህጉሩ ጋር ያለው ግንኑነት የሚያድግበት መንገድ መሆኑን ገልጸው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይህም የእስራኤልና የአፍሪካ ግንኙነት የሚከበርበት እንደነበር ገልጸው ነበር፡፡