አፍሪካ የመጀመሪያውን የወባ ክትባት ለማግኘት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር እየመከረች ነው
በአፍሪካ በየአመቱ ሩብ ሚሊዮን ህጻናት በወባ በሽታ ህይወታቸውን ያጣሉ
የወባ መከላከያ ክትባት ፍላጎት በፈረንጆቹ 2030 በዓመት እስከ 100 ሚሊየን ክትባት ሊያድግ ይችላል
አፍሪካ የመጀመሪያውን የወባ ክትባት ለማግኘት ከአለም የጤና ድርጅት ጋር እየመከረች መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
በመጀመሪያ ደረጃ የመድሃኒቱ አቅርቦት መኖሩን ለማረጋገጥ ከድርጅቱና ከክትባት ጥምረት ጋር እንደሚመክሩ የአፍሪካ የበሽታመቆጣጠርና መከላከል ማእከል ዳይሬክተር ጆን ንጋስሶንግ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት ድርጅቱ አርቲኤስ እስ ወይሞ ሞስኪርይክስ የተባለዉና በእግሊዙ የመድሃኒት ማምረቻ ኩባንያ የሚመረቱውን መድሃኒት ለአፍሪካ ህጻናት መሰጠት አለባቸው ማለቱን ተከትሎ ነው።
ባለሙያዎች እንዳሉት በየአመቱ በአፍሪካ ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት ለሚገድለው በሽታ መድሃኒቱ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሏል።
የወባ በሽታ በአፍሪካ ትልቅ ገዳይ ነው ያሉት ኔንጌሶንግ መድሃኒቱ ለአፍሪኬ ሀገራት መቼ እንደሚደርስ ግልጽ አልነበረም፤ ዋጋውም ውድ በመሆኑ የሚመረትበት ፍጥነትም አይታወቅም ብለዋል።
የመድሃኒት አምራቹ ኩባንያ እስካሁን እስከ ፈረንጆቹ 2028 ድረስ 15 ሚሊዮን ሞስኩሪክስ መጠን ለማምረት ማቀዱን አስታውቋል።
በአለም ጤና ድርጅት የተጠናው ጥናት እንደሚያመለክተው የወባ ክትባት ፍላጎት በፈረንጆቹ 2030 በአመት ከ50 ወደ 100 ሚሊየን ክትባት ያድጋል።