ብዙ የጎዳና ተዳዳሪ ዜጎች የሚገኝባቸው የአፍሪካ ሀገራት
በናይጀሪያ 24 ሚሊዮን ዜጎች ኑሯቸውን በጎዳናዎች ላይ ይመራሉ ተብሏል
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ እና ሱዳን በመቀጠል በስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
ብዙ የጎዳና ተዳዳሪዎች የሚገኝባቸው የአፍሪካ ሀገራት
ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ እንደዘገበው ከሆነ በአፍሪካ ህይወታቸውን በጎዳናዎች ላይ ያደረጉ ዜጎች ከፍተኛ ነው።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የራሳቸው ቤት የሌላቸው አልያም ተከራይተው መኖር የማይችሉ ወይም የሚያስጠልላቸው ሰው የሌላቸው ሰዎች ህይወታቸውን በጎዳናዎች ላይ ያደርጋሉ።
በዚህም መሰረተ በናይጀሪያ 24 ሚሊዮን ዜጎች ህይወታቸውን በጎዳናዎች ላይ ተጠልለው ሲመሩ 12 ሚሊዮን ግብጻዊያንም እንዲሁ በተመሳሳይ ይኖራሉ።
በነዳጅ የበለጸገችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሶስተኛነት ስትቀመጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ ቤት አልባ ናቸው።
በአራተኛነት እና አምስተኛነት የተቀመጡት ደግሞ ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ እና ሱዳን ናቸው።
በኢትዮጵያም 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች በተሙሳሳይ ቤት ውስጥ መኖር የማይችሉ ናቸው ተብሏል።