የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በአስመራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ኤርትራ አስታወቀች
የማነ በኤክስ ገጻቸው እንደገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳያስ እና ሊቀመንበሩ መሃመት አህጉሪቱ እያጋጠሟት ባሉት ፈተናዎችና የወደፊት እቅዶች ዙረያ ዝርዝር ውይይት አድርገዋል
ከኢትዮጵያ ከተገነጠለችበት ከ1991 ጀምሮ መንግስት ቀይራ የማታውቀው ኤርትራ በሰብአዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባት ሀገር ነች
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በአስመራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ኤርትራ አስታወቀች ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት የተመራ የልኡክ ቡድን በአስመራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ውውይት ማድረጉን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል።
የማነ በኤክስ ገጻቸው እንደገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳያስ እና ሊቀመንበሩ መሃመት አህጉሪቱ እያጋጠሟት ባሉት ፈተናዎችና የወደፊት እቅዶች ዙረያ ዝርዝር ውይይት አድርገዋል።
ሊመንቀሩ የአፍሪካ እድገት በተወሰኑ የአህጉሪቱ ቀጣናዎች ባሉ የጸጥታ እና አለመረጋጋት ችግሮች እክል እንደገጠመውና ይህም በውጭ ጣልቃ ገብነት መባባሱን መናገራቸውን የማነ ገልጸዋል።
ነገርግን ሚኒስተሩ ለእድገት እንቅፋት የሆኑት እና ውይይች የተደረገባቸውን ግጭቶች በዝርዝር አልጠቀሱም።
ሚኒስትሩ እንዳሉት አባል ሀገራት የሚጠበቅባቸውን አመታዊ መዋጮ መክፈል አለመቻላቸው የአፍሪካ ህብረት በራሱ ሀብት እንዳይተማመን ማድሩንም ሊቀመንበሩ በውይይቱ ወቅት አንስተዋል።
ፕሬዝደንት ኢሳያስም የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን መፈታት አለበት የሚለውን መርህ እንደሚደግፉና ዘላቂ ልማት ያለ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት የማይሳካ መግለጻቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን ሀብት በመጠቀም የጋራ ፕሮግራም ላይ እንዲያተኩሩ እንዲሁም ህብረቱም አፈጻጸሙን ለማሻሻል የመዋቅር ክላሳ እንደሚያስፈልጋቸው መጥቀሳቸውን የማነ ገልጸዋል።
ስለጉብኝቱ ህብረቱ ያወጣው መግለጫ የለም።
ከኢትዮጵያ ከተገነጠለችበት ከ1991 ጀምሮ መንግስት ቀይራ የማታውቀው ኤርትራ በሰብአዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባት ሀገር ነች።
ይሁን እንጅ ውስጣዊ ግጭቶች አይሰተዋሉባትም።
በአፍሪካ በተለይም በምስራቁ ቀጣና በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በሶማሊያ የሰዎችን ህይወት የሚቀጥፉ ግጭት እየተካሄዱ ይገኛሉ።